Stationery
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 021/18
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል።
- በጨረታ እንደ (ሎት 1) - Plate Cleaner (የፕሌት ማፅጃ) ብዛት 300 ሊትር ግዥ
- በጨረታ ሁለት (ሎት 2) ፦ የዕቃ ማሰሪያ ቃጫ (Suring for Packing) ብዛት 1,500 ኪ.ግ ግዥ፣
- በጨረታ ሶስት (ሎት 3) ፦ክር (Cotton Thread 5,000mts) ብዛት 200 ግዥ፤
- በጨረታ አራት (ሎት 4) - የፅህፈት መሳሪያዎች ግዥ ማለትም፡- Computer Paper (የኮምፒውተር ወረቀት) ብዛት 2,000 ፓኬት Blue Ball Point Pen (ሰማያዊ እስክሪቢቶ) ብዛት 7,000 Red Ball Point Pen (ቀይ አስክሪቢቶ) ብዛት 1,000፣ Pencil (እርሳስ) ብዛት 500፣ Marking Pen (ማርከር) ብዛት 5,000 Box file (ፋይል አቃፊ) ብዛት 1,900 Scotch Tape Cheque packing big (ፕላስተር ትልቁ) ብዛት 1,000 ጥቅል Correcting Fluid (ፍሉድ) ብዛት 300 ቦትስ Paper Clips 33mm (አግራፍ) ብዛት 300 ፓኬት፤ Rubber Band (የብር ማሰሪያ ላስቲክ) ብዛት 500 ኪ.ግ ፣ የፅዳት መሳሪያዎች ግዥ ማለትም ፤ ባለ 200 ግራም ሳሙና ብዛት 6,000, ቁርጥራጭ ጨርቅ (Hag) ብዛት 2,000 ኪ.ግ፤ ባለ 500 ግራም ቪም ብዛት 300 ቲን፣ ዲቶል (Detol 500ml) ብዛት 400 ቦትል Powder Soap (ባለ 200 ግራም የዱቄት ሳሙና) ብዛት 3,000 ፓኬት እና መወልወያ (Floor Clearing Rag) ብዛት 200 በጨረታ አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ከሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሺያል የቴከኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው::
ጨረታው 19/01/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በገዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሰነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ ገጽ (www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-09-29
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-29 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Berhanena Selam Printing Enterprise
- Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
- Posted at: 2026-08-31T09:39:58.000Z