Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በምስራቅ ወለጋ ዞን የኪረሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 የበጅት ዓመት በወረዳው ላሉት የመንግስት መ/ቤቶች ለ2019 የበጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፤ የአሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ሞተር ሳይክሎች፤ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛና የግንባታ ዕቃዎች፤ የመኪናና ሞተር ሳይክል ጎማዎች፤ የሠራተኛ ደንብ ልብስ እና ለሎች የተለያዩ ዕቃዎችን
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ወለጋ ዞን የኪረሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 የበጅት ዓመት በወረዳው ላሉት የመንግስት መ/ቤቶች ለ2019 የበጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፤የአሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ሞተር ሳይክሎች፤ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛና የግንባታ ዕቃዎች፤ የመኪናና ሞተር ሳይክል ጎማዎች፤ የሠራተኛ ደንብ ልብስ እና ለሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር (2018-2019) የከፈሉ፤ በተጨማሪ እሴት ታክስ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ቲን ቁጥር ያላቸው::
2. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ከ24/12/2018 ዓ.ም እስከ 08/01/2019 ዓ.ም ድርስ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ/ ብር ከፍለው ከኪረሙ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ክፍያ በመክፈል ከወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቀጥር 5 መዉሰድ ይችላሉ ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ ብር በእያንዳንዱ የንግድ ዘርፍ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፐኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
4. ተጫራቾች ጨረታውን አሸንፈው ዕቃውን ለማቅረብ የውል ማስከበሪያ ዋጋ የአቅራቦቱ 10/100 የማስያዝ ግዴታ አለበት።
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
6. ተጫራቾች የዕቃዉን ዋጋ ዝርዝር የተጠየቀውን (ስፔስፊኬሽን) ሳይለውጡ የጨረታ ማወዳደሪያ በቀረበው ሰነድ ላይ ዋጋው ከነተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ በመሙላት፤ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሳቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያዩ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 08/01/2019 ዓ.ም ድረስ በቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው ሳጥን ጨረታው ከመዘጋቱ ከ 11፡00 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ09/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ በ 3፡00 ላይ ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
8. የጨረታው ሣጥን ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ፡፡
9. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን የዕቃ ዝርዝር ጥራታቸውንና ብዛታቸውን ጠብቆ ከውል ሰጭ መ/ቤት በሚያደርገው የውል ስምምነት መሰረት ኪረሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሚገኘው የውል ሰጪ መ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል ፡፡
10. መ/ቤታችን በሚያወዳድረው ዕቃዎች ብዛት ላይ እንደ አስፈላጊነቱ 20/100 መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር- 0920 409 064/ 0926 364 774
በምስራቅ ወለጋ ዞን የኪረሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-18
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-09-19 09:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Kiremu Woreda FEDB
- Bid bond: 30,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
- Posted at: 2026-08-31T09:47:37.000Z