House and Building Sale

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. መኖሪያ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. (በቀድሞ ስሙ ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ) ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ሥልጣንና ውክልና መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

.

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

አበዳሪውቅርንጫፍ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የቦታው ስፋት

የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር

የንብረቱ

ዓይነት

የጨረታው መነሻ ዋጋ /ብር/

ጨረታ የሚከናወንበት

ከተማ

/ከተማ

ቀበሌ

ቀን

ሰዓት

1

አቶ ዳግም ቴዎድሮስ ተሾመ

 

 

ተበዳሪው

አዳማ

አዳማ

ደንበላ

09

619.96 ካሬ ሜትር

OR001090302011

 

B+G+1 ቪላ የንግድ

 

19,837,223.77

28/01/2019 .

ከጠዋቱ 400-5:30

2

ሪኖ ዋን ትሬዲንግ /የተ/የግ/ማህበር

አቶ ሀብታሙ አበራ በቀለ

ወሰን

አቃቂ ቃሊቲ

02

229 ካሬ ሜትር

AA000070203259

G+2 ለመኖሪያ

22,966,426.77

29/01/2019 .

ከጠዋቱ 400-5:30

የጨረታ ደንቦች፡–

  1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) በማስያዝ መመዝገብ ይችላሉ።
  2. የተጫራቾች ምዝገባ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል። በጨረታው የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም።
  3. ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ይካሄዳል።
  4. በጨረታው ላይ ተጫራቾች፣ አስያዥና ተበዳሪ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ። ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፡፡
  5. የንግድ ማህበራትን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ የያዘና በማሀበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።
  6. የጨረታው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ የተገለጸለት ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። ባይከፍል ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
  7. በንብረት ማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የሊዝ ክፍያ ወይም ሌላ ማንኛውንም ክፍያ ገዢው ይከፍላል።
  8. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
  9. ለበለጠ ማብራሪያ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዋናው መሥሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 011 5 31 81 17 (የህግ አገልግሎት መምሪያ) ወይም 0221 11 84 71/72 (አዳማ ቅርንጫፍ) ወይም 0116-68-09-61 (ወሰን ቅርንጫፍ) ደውሎ መጠየቅ ወይም አበዳሪውን ቅርንጫፍ በአካል ቀርቦ ማነጋገርና ንብረቱን የሚጎበኙበት ሁኔታ ማመቻቸት ይቻላል።
  10. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Tender details

  • Deadline: 2026-10-09
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-09 11:30
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Global Bank Ethiopia S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Aug 30, 2026)
  • Posted at: 2026-08-31T13:30:24.000Z
← Back to all tenders