Musical Instruments

አማራ ባንክ አ.ማ. የመድረክ የሳውንድ ሲስተም፣ የስክሪን አቅርቦት፣ ቀጥታ ስርጭት እና ዶክመንቴሽን እና የተለያዩ ህትመቶች፣ ቲሸርት እና ባነር ህትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

 ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር- አባ/ግፋማመ/ሀግጨ/034/2026

(1) አማራ ባንክ አማ ህዳር 27 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ለሚያካሄደው የባለአክስዮኖች ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ ለሚደረግ ሁነት ዝግጅት ግብዓት ሆነው የሚያገለግሉ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተጠቀሱትን የተለያዩ አገልግሎት እና አቅርቦቶችን በብቃት መፈፀም የሚችሉ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

የአገልግሎት ዓይነት

ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1

የመድረክ የሳውንድ ሲስተም፤የስክሪን አቅርቦት፤ ቀጥታ ስርጭት እና ክመንቴሽን፣

መስከረም 7 ቀን 2019 .. እስከ 800 ሰዓት

መስከረም 7 ቀን 2019 .. እስከ 830 ሰዓት

200,000.00

ሎት 2

 

የተለያዩ ህትመቶች፣ ቲሸርት፣ እና ባነር ህትመት

መስከረም 7 ቀን 2019 .. እስከ 830 ሰዓት

መስከረም 7 ቀን 2019 .. እስከ 900 ሰዓት

50,000.00

(2) ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከለገሃር ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በሚወስደው መንገድ መብራቱን እንደተሻገሩ የአመልድ ህንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋሲሊቲዎች አስተዳደር መምሪያ 20ኛ ወለል ላይ ከነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ) የምድር ወለል ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።

(3) ተጫራቾች ከጨረታው በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ከላይ በተገለፀው መሠረት ከጨረታው መክፈቻ ቀን ጀምሮ ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲፒኦ ወይም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሚሰጥ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በአማራ ባንክ አ.ማ. ስም አስርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

(4) ተጫራቾች የሙያ ፈቃድ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

(5) ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት መሠረት ማስገባት አለባቸው። ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

(6) የጨረታው ሰነድ አማራ ባንክ አ.ማ. 20ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት መግባት ይኖርበታል።

(7) ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት አማራ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋሊቲስ መምሪያ 20ኛ ፎቅ ይከፈታል።

(8) ከላይ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች አለማሟላት ከጨረታው ውጭ (ውድቅ) ያስደርጋል።

(9) ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011558-29-05 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

(10)ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አማራ ባንክ አ.ማ

ከባንክ ባሻገር!


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-17 15:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Amhara Bank S.C.
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Reporter (Aug 30, 2026)
  • Posted at: 2026-08-31T14:06:43.000Z
← Back to all tenders