Vehicle (garage service)

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ማሽነሪዎች እና መኪኖች አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት አመት ለገላን ከከተማ ለማዘጋጃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎች እና መኪኖች አወዳድሮ ማስጠገን ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ /መረጃዎች በማቅረብ/ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፍ ይጋብዛል፡፡

1- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡

2- አቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣

3- ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin/ተመዝጋቢ የሆነ፡፡

4- የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

5- ከትራንስፖርት ቢሮ የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ(ሰርተፊኬት) እና ደረጃ 2(ሁለት)ፍቃድ ያለው መረጃ ማቅረብ የሚችል

6- መስሪያ ቤቱ በሚፈልግበት ቦታ (መኪና ወይም ማሽነሪዎቹ ተበላሽቶ የቆሙበት ቦታ)ሄዶ መጠገን ወይም መስራት የሚችል

7- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15 ተከታታይ የስራ ቀናት እና በስራ ሰዓት ለያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1500.00 (አንድ ሺ አምስት መቶ ብር) በአካውንት ቁጥር 1064934721214 በማስገባት በገላን ክ/ከተማ ገቢዎች ባለስልጣ ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ ፡፡

8- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ( 15) ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡

9- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ (ተዘግቶ ልክ በዚሁ ቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡

10- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000 (አምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

11- ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡

12- ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል ፡፡

13- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ ቦኋላ በጨረታው ሰነድ ለይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይችልም፡፡

14- የመወዳደሪያ በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል ፡፡

15- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

16- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 4 45 01 82 (09-23 57 49 41) በመደወል እና በአካል ተገኝቶ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት/ገላን

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-17 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Sheger City Administration Gelan Sub City Finance Office
  • Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: ለያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1500.00 (አንድ ሺ አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T07:45:09.000Z
← Back to all tenders