Stationery

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት  ዓመት ከዚህ በታች ከሎት 1 እስከ ሎት 15 የተከፋፈሉ ግዥዎች  በግልጽ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት

የሚገዛው ዕቃዎች ጥገና አገልግሎት

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን CPO

ናሙና

ሎት 1

አላቂ የቢሮ እና የጽህፈት መሣሪያዎች

6,000 CPO

ማቅረብ አለባቸው

ሎት 2

የደንብ ልብስ ግዥ

6,000 CPO

ማቅረብ አለባቸው

ሎት 3

አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ግዥ

6,000 CPO

ማቅረብ አለባቸው

ሎት 4

የደንብ ልብስ ስፌት

2,000 CPO

ማቅረብ አለባቸው

ሎት 5

የህንፃ መስሪያ ዕቃዎች

3,000 CPO

ማቅረብ አለባቸው

ሎት 6

የስፖርት ዕቃዎችና መገልገያዎች

3,000 CPO

ማቅረብ አለባቸው

ሎት 7

የህክምና እቃ

3,000 CPO

ማቅረብ አለባቸው

ሎት 8

የላብራቶሪ መገልገያ

3,000 CPO

ማቅረብ አለባቸው

ሎት 9

የህንፃ ጥገና አገልግሎት

5,000 CPO

አያስፈልግም

ሎት 10

የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት

5,000 CPO

አያስፈልግም

ሎት 11

የሰራተኛ ቁርስ መስታንግዶ ካፌ

3,000 CPO

አያስፈልግም

ሎት 12

የህትመት ስራ

3,000 CPO

ማቅረብ አለባቸው

ሎት 13

የቋሚ እቃ / የፈርኒቸር ግዥ

5,000 CPO

ማቅረብ አለባቸው

ሎት 14

የቋሚ እቃ /የኤሌክትሮኒክስ ግዥ

5,000 CPO

ማቅረብ አለባቸው

ሎት 15

የህዝብ ማመላለሻ እና የጭነት መኪና ኪራይ

2,000 CPO

አያስፈልግም

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

  1. ለሁሉም ሎት በዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና ጨረታ ለመወዳደር የሚገልፅ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  3.  ከሎት11 በስተቀር የአቅራቢዎች የምስክር ወረቀት እናየቫት /VAT/ ተመዝጋቢነቱ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
  4. ለሎት11 የሰራተኛ ቁርስ መስተንግዶ ካፌ ብቻ የቲኦቲ ወይም የቫት ተመዝጋቢ የQRኮድ ደረሰኝ ያለው መወዳር ይቻላል።
  5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30 እስከ11፡00  በቃሌ ቅድመ1 ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት ሁለት መቶ (200) ብር በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲን (CPO) በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
  7. ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን በመሙላት ኦርጅናል ፋይናንሻል፣ ቴክኒካል ሰነድ እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ የሎት ዓይነት በመግልፅ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች የዕቃዎችን ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
  11. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን፤ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው፤
  12. የዕቃ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ማሟላት አለባቸው፣ ሰነዶቹ በማህተም መረጋገጥ አለባቸው።
  13.  አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዕቃዎች ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
  14.  ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑና የጨረታ ማስከበሪያው ማስከበሪያው (CPO) እንደሚወረስባቸው ማወቅ ይኖርባቸዋል።
  15. ለአገር ውስጥ ተጫራቾች ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅት ከሆነ መጫረት የሚችሉት በተደራጁበት ምርት ውጤት ብቻ ሲሆን ከአደራጃቸሁ መስሪያ ቤት የጨረታ ማስከበሪያው ደብዳቤ የሚደረግላቸው ይሆናል። በማቅረብ በራሱ አምራች ድርጅት 3% አስተያየት ሚደረግላቸው ይሆናል።
  16. አሸናፊ ድርጅት እቃውን በራሳቸው ትራንስፖት የት/ቤቱ ንብረት ከፍል ማስገባት አለበት።
  17. የዕቃ ብዛት 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ አውቆ የመጫረት ግዴታ አለበት።
  18. ለአንድ እቃ ሁለት አይነት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ አይቻልም
  19. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት አስኮ እየሱ ፀበል በአክሱም አዳራሽ 400 ሜትር ገባ ብሎ

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁ 011 2 73 17 69 በጉ/ክ/ አ/ወ/ 05 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

በጉለሌ  ክፍለ ከተማወረዳ 05 ቃሌ  ቅድመ 1ኛ፣1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-12 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kale Kindergarten & Elementary School
  • Buyer address: አስኮ እያሱ ፀበል በአክሱም አዳራሽ 200 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T09:16:32.000Z
← Back to all tenders