Stationery

በምስራቅ ወለጋ ዞን የጉቶ ጊዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉት የመንግስት መ/ቤቶች ለ2019 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በምስራቅ ወለጋ ዞን የጉቶ ጊዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉት የመንግስት መ/ቤቶች ለ2019 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል

  • አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣
  • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
  • የሠራተኞች ደንብ ልብስና የስፌት ዋጋ፣
  • የመኪና ጎማ እና መኪና ጥገና አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

1. በዘርፉ 2018/2019 ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡ የዘመኑ፤ ግብር፤ የከፈሉ፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ከ20/12/2018ዓ.ም እሰከ 6/1/2019 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ ብር 150 (መቶ ሃምሳ ብር) በእያንዳንዱ የንግድ ዘርፍ ከፍለው ከጉቶ ጊዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ከሙስና የፀዱ መሆን አለባቸው።

4. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 (መቶ ሺህ ብር) ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት።

6. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዋጋ ዝርዝር የተጠየቀውን “Specification” ሳይለውጡ የጨረታ ማወዳደሪያ በቀረበው ሠነድ ላይ ዋጋው ከነተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በመሙላት ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማሰፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያዩ በስም ከታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ በኤንቨሎፕ ታሽጎ እስከ /01/2019 ዓ.ም ድረስ በቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው ሣጥን ጨረታው ከመዘጋቱ ከ5፡30 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 11/1/2019 ዓም. ከሰዓት በኋላ በ7፡30 ሰዓት ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።

8. የጨረታው ሣጥን ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

9. የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ዕቃዎቹን ከውል ሰጪው መ/ቤት ጋር በሚያደረገው የውል ስምምነት መሠረት ነቀምት በሚገኘው በውል ሰጭው ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል።

10.ተጫራቾች ዕቃዎቹን አሸንፈው ለማቅረብ ሲዋዋሉ የውል ማሰከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

11.መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ- 0576602540

በምስራቅ ወለጋ ዞን የጉቶ ጊዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-21
  • Bid closing time: 13:30
  • Bid closing (note): የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያዩ በስም ከታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ በኤንቨሎፕ ታሽጎ እስከ /01/2019 ዓ.ም. ከ5፡30 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል
  • Bid opening: 2026-09-21 13:30
  • Bid opening (note): 11/1/2019 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በ7፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: East Wollega Zone Guto Gida Woreda FEDB
  • Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
  • Bid document price: 150.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T10:07:56.000Z
← Back to all tenders