Building Construction

በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መር ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት የ1ኛ ደረጃ ት/ቤት 2(ሁለት) ብሎክ የተማሪዎች መማሪያ እና 1(አንድ)ብሎክ የቢሮ አገልግሎት የሚሰጥ ህንጻ በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 01

ማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መር ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2019 በጀት አመት በወረዳው ማእከል ሚቄ ከተማ የ1ኛ ደረጃ ት/ቤት 2(ሁለት) ብሎክ የተማሪዎች መማሪያ እና 1(አንድ)ብሎክ የቢሮ አገልግሎት የሚሰጥ ህንጻ በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ስለፈለገ በዘርፉ ፈቃድ ያለው ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት መስፈርቶችን የሚያሟላ ድርጅት እንዲወዳደር ይጋብዛል፡፡

መስፈርት፡-

  1. በዘርፉ ደረጃ 6(ስድስት) ፈቃድ ያለው እና ፈቃዱን ያደሰ መሆን አለበት
  2. የዘመኑ ግብር የከፈለ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ተመዝጋቢ የሆነ
  3. የአቅራቢነት ምዝገባ በኦንላየን የተመዘገበ
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / TIN Number/ ያለው
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሚውል 300,000/ሶስት መቶ ሺ ብር/Unconditional(በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ) ሲፒኦ ወይም ቢድቦንድ ማቅረብ የሚችል በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ከጉራጌ ዞን እኖር ኤነር ምገር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግ/ን/አስ ስራ ሂደት 500( አምስት )መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላል፡፡ ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ለተከታታይ ለ15(አስራ አምስት) የስራ ቀናት ብቻ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ደግሞ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋጋ ሞልተው ኣንድ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ፋይናሻል ኦርጂናል እንዲሁም ሁለት ኮፒ በማዘጋጀት በፖስታ በማሸግና በእናት ፖስታ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ቢያጋጥም በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚሻገር መሆኑን እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-በአፈፃጸማቸው ምክንያት ከክልሉ ግዥ ኤጀንሲ እገዳ ወይም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መወዳደር አይችሉም፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- እኖር ኤነር መገር ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ለተከታታይ ለ15(አስራ አምስት) የስራ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-16 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ለተከታታይ ለ15(አስራ አምስት) የስራ ቀናት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Enor Ener Mager Woreda FEDB
  • Bid bond: 300,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T11:11:28.000Z
← Back to all tenders