Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የሻሸመኔ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሻሸመኔ ከተማ የመንግስት መ/ቤቶች ለ2019 በጀት አመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የግዥ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

የሻሸመኔ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሻሸመኔ ከተማ የመንግስት መ/ቤቶች ለ2019 በጀት አመት በ1ኛ ዙር ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት አንድ (1) የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች
  • ሎት ሁለት (2) አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት ሶስት (3) የቢሮ የጽዳት እቃዎች
  • ሎት አራት (4) የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች
  • ሎት አምስት (5) ቋሚ የቢሮ እቃዎችን(ፈረኒቸሮች)
  • ሎት ስድስት (6) የቀላል እና ከባድ መኪና ጎማዎች
  • ሎት ሰባት (7) ሞተር ሳይክል

ስለዚህ ዕጩ ተጫራቾች ሊያውቁት የሚገባቸው መመሪያ፡-

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገቡ እና ሕጋዊ የሆነ የታደሰ የ2018/2019 ዓ.ም የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና ግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (TIN No.) ያለቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የመንግሥት ግዥ ላይ ለመሳተፍ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክ (VAT) የግብር ከፋይነት የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. መስሪያ ቤታችን የተጨማሪ ከእሴት ታክስ (VAT %5) 50%ቱን ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

5. እያንዳንዱ ተጫራች ከላይ በየሎቱ ለተዘረዘሩት እቃዎች በየሎቱ በተጠቀሰው መሰረት ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች ብቻ ለብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የኢትዮጵያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ጋራ ማስያዝ አለባቸው፤ አዲስ የማይክሮ ድርጅቶች ኦሪጅናል የዋስትና ደብዳቤ በህጋዊነት ካደራጃቸው አካል ማቅረብ አለባቸው።የዋስትና ደብዳቤው የሚያገለግለው አዲስ ለተደራጁ ማይክሮዎች ብቻ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።

6. ተጫራቾች በሚያቀርቡአቸው ፖስታዎችም ላይ የሚወዳደሩባቸውን ሎቶች ቁጥራቸውን እና አይነት መፃፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ ሰነድ በየሎቱ ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ለየብቻ ወይንም በተናጠል የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት በሻሸመኔ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት ቀርበው መውሰድ  ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ዋጋ ቦታ በነጠላ ዋጋ መግለፅ እና በጥንቃቄ ቫትን (VAT) 15%) ጨምሮ በመሙላት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያየ በታሸጉ ፖስታዎች ውስጥ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።

9. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመጫረቻ ሰነድ በታሸገ ኤንቬሎፕ ዋና እና ኮፒ በሻሸመኔ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ታከተተይ የስራ ቀናት ከጦዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን ከጦዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር በሻሸመኔ ከተማ ገንዘብ ጽ/ ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት ክፍል ይከፈታል፤ ካልተገኙም ጨረታው አይደናቀፍም።ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል።

10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ስማቸውንና አድራሻቸውን በግልጽ መጻፍ እና የድርጅታቸውን ማህተም ማሳረፍ ይኖርባቸዋል።

11. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ4 ቀናት ውስጥ በሻሸመኔ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በመቅረብ ካሸነፈው ዕቃ ላይ አስር ፐርሰንት/10%/ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የዕቃዎቹን ናሙና በመያዝ ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል።

12. በተራ ቁጥር 11 ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ውል የማይፈጽም አሸናፊ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ በመሆን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ይችላል።

13. አሸናፊ አቅራቢዎች ውል ተፈራርመው እስከ 15/አስራ አምስት ቀን ከላይ በተገለጸው አድራሻ በራሳቸው መጓጓዣ ዕቃዎቹን ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

14. በጨረታው ላይ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ለስልሳ) ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።

15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብረሪያ የሻሸመኔ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በማቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0964817771/ 099325977 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ

የሻሸመኔ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ተከተተይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-09-17 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ተከተተይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Shashemene City Finance Office
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T11:40:10.000Z
← Back to all tenders