Equipment and Accessories

የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ በዋናው መ/ቤት የሚገኙ ያገለገሉ ኮምፒውተሮችና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ያገለገሉ ፈርኒቸሮች፣ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎችና ባትሪዎች፣ የብረታ ብረት ስክራፖች እና የወላለቁ ፈርኒቸሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር- መኢኢግ/ንአኮ/001/2018

የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ በዋናው መ/ቤት የሚገኙ ያገለገሉ ኮምፒውተሮችና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ያገለገሉ ፈርኒቸሮች ያገለገሉ የመኪና ጎማዎችና ባትሪዎች የብረታ ብረት ስክራፖች እና የወላለቁ ፈርኒቸሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።

  • ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች ህጋዊ አሰራርን ተከትለው የሚሰሩ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ የሚከተሉትን ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው።

  • የታደሰ የንግድ ፈቃድ: ለሚወዳደሩበት የሥራ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድ።
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Certificate): የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት።
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰነድ: (እንደ ጨረታው መጠንና መስፈርት)። 
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
  • የግብር ክሊራንስ (Tax Clearance Certificate): ግብር ከፍለው ማጠናቀቃቸውን የሚያሳይ ወቅታዊ ደብዳቤ።

2. ለጨረታ የሚያስፈልጉ ቅጾች የሚገኙበት ዝርዝር፡-

/

የሎት ማጣቀሻ

የንብረቶች ዓይነትና ሰነዱ የሚገኝበት ዝርዝር

መግለጫ

1

ሎት 1

ያገለገሉ ኮምፒውተሮችና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

ባሉበት ሁኔታ በቁጥር የሚሸጡ ናቸው።

2

ሎት 2

ያገለገሉ ፈርኒቸሮች

የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች ባሉበት ሁኔታ በቁጥር የሚሸጡ ናቸው።

3

ሎት 3

 

ያገለገሉ የመኪና ጎማዎችና ባትሪዎች

የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎችና ባትሪዎች ባሉበት ሁኔታ በቁጥር የሚሸጡ ናቸው።

4

ሎት 4

 

የብረታ ብረት ስክራፖች እና የወላለቁ ፈርኒቸሮች

 

ቁርጥራጭ ብረታብረቶች፤ የተለያዩ ስክራፕ የተሽከርካሪ አካላቶች እና የወላለቁ ፈርኒቸሮች ባሉበት ሁኔታ በኪሎ እና በሜትር ኩብ የሚሸጡ ናቸው።

3. ከዚህ በላይ በቀረበው ዝርዝር መሠረት በግንባር ቀርበው ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ የተቋሙን የቃለ ማላ ፎርሞች እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ 500.00 ብር (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በመግዛት ማግኘት ይችላሉ፤

4. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ በመያዝ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ በተከታታይ የመንግስት የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን የሚገኙበት ቦታ መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ (መኢኢግ) ዋናው መ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሀይሌ ጋርመንት በመምጣት መመልከት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር(በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መጠን) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ (መኢኢግ) ስም ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል ነገርግን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) ያላስገባ (ያልያስያዘ) እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ወዲያውኑ ውድቅ ይደረጋል።

6. ጨረታው ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምሰት) የመንግስት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ሲሆን ጨረታው በ 16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በገዙበት ተቋም በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። እንዲሁም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።

7. የመከላከያ ኢንጂነሪግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ (መኢኢግ) ያወጣውን ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።

8. የጨረታው አሸናፊዎች ተለይተው ከታወቁ በኋላ ለተሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያውኑ የሚመለስላቸው ሲሆን ለአሸናፊ ተጫራቾች ውል ከተፈራረሙ በኋላ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያውኑ ይለቀቅላቸዋል ወይም እንደ ፍላጎታቸው ጠቅላላ የውል ዋጋው ላይ ሊደመርላቸው ይችላል።

9. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፤

10. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የመንግስት የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ (መኢኢግ) ዋናው መ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሀይሌ ጋርመንት ንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።

11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ጨረታው ከመዘጋቱ 5 ቀን በፊት በጽሁፍ ወይም በስልክ ቁጥር (09 10 41 24 94/ 09 33 66 65 39) ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

12.ግሩፑ ጨረታውን የተሻለ መንገድ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በ 16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-17 14:30
  • Bid opening (note): በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በ 16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ/መኢኢግ/
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T11:40:39.000Z
← Back to all tenders