Equipment and Accessories

በየካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አላቂ ማሰልጠኛ፣ አላቂ የፅዳት፣ አላቂ የህትመት፣ አላቂ የህክምና የሚውሉ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/2019

በየካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም በጨረታ ቁጥር001/2019 ዓ.ም በጀት ዓመት አላቂ ማሰልጠኛ፣ አላቂ የፅዳት፣ አላቂ የህትመት፣ አላቂ የህክምና የሚውሉ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1 አላቂ የማሰልጠኛ ዕቃዎች…………………………….50,000.00
  • ሎት 2 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች……………………………………20000.00
  • ሎት 3 አላቂ የህክምና ዕቃዎች……………………………….20000.00

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱት መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ህጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያለው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈለ
  3. በመንግስት ግዢ ኤጀንሲ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገበበትን ኮፒ ማቅረብ የሚችል
  4.  ተጨማሪ የእሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  5.  ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በእያንዳንዱ ሎት 500 ብር በመክፈል የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ከግዢ ክፍል መውሰድ ይቻላል፡፡
  6.  ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ኦሪጅናልና ኮፒ ማስገባት አለበት፡፡ ሰነዱ ላይ ፊርማና ክብ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች ከላይ በየሎቱ የተጠቀሱት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
  8.  ናሙና የሚያስፈልጋቸው የዕቃ አይነቶች ናሙና ማቅረብ፣ በናሙናው ለማቅረብ የሚያስቸግሩትን በፎቶ ጨረታው ከመዘጋቱ ቀደም ብሎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙናዎቹ ለተሸነፉ ተጫራቾች ተመላሽ ይሆናል፡፡
  9. የጥቃቅንና አነስተኛ አቅራቢዎች በሚያመረቱት ምርት ብቻ በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑ አንዲሁም ከሚመለከተው አካል ለኮሌጁ ስም የተጻፈ ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  10. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ ኮሌጁ ድረስ በማምጣት በኮሌጁ ንብረት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርበታል
  11. ጨረታው ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ልክ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  12. አሸናፊው ውል ገብቶ ዕቃዎችን ከማስገባት በፊት ውል የመሰብሰቢያ 10 በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  13. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14.  ት/ቤቱ አሸናፊው ድርጅት ላሸነፈባቸው ዕቃዎች 20/100 ብዛት ከውል በፊት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው፡፡
  15. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያ መሠረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

አድራሻ፡- ፈረንሳይ ለጋሲሆን ታክሲ ማዞሪያ ከፍ ብሎ የድሮ ካራማራ ት/ቤት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-1-54-99-36/011-1-14-49-05

የየካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-12 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yeka Industrial College
  • Buyer address: የካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፈረንሳይ ለጋሲዮን ታክሲ ማዞሪያ ከፍ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T12:10:04.000Z
← Back to all tenders