Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ 10 የገላን ጉራ ቅድመ መጀመሪያ፣ መጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 003/2019ዓ.ም

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ 10 የገላን ጉራ ቅድመ መጀመሪያ፣ መጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ

  • ሎት 1፡- ደንብ ልብስ፣
  • ሎት 2 ፡ የፅዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት 3፡- አላቂ ቢሮ ዕቃዎች፣
  • ሎት 4፡_ አላቂ የትምህርት ዕቃ፣
  • ሎት 5፡- ህትመት፣
  • ሎት 6፡- ትራንስፖርት አገልግሎት፣
  • ሎት 7፡- ቋሚ ዕቃ እና
  • ሎት 8፡- ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

1. የዘመኑን በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው።

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

3. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።

4. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለ መሆናቸው ማስረጃ ከ(EGP/ www.PPA.GOV.ET) ፕሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ ከላይ የተዘረተዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና እንዲሁም ናሙና ለሚጠይቁ ዕቃዎች ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ናሙና ማቅረብ የሚችል።

5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ በየሎቱ 1.5% ሎት 1 ደንብ ልብስ 34,500፣ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች 20,700፣ ሎት 3 አላቂ  ቢሮ ዕቃዎች 12,000፣ ሎት4 አላቂ የትምህርት ዕቃ 13,500፣ ሎት5 ህትመት 900፣ ሎት 6  ትራንስፖርት አገልግሎት 2,200፣ ሎት7 ቋሚ ዕቃ 575 እና ሎት 8 ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች 575 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ትዕዛዝ (CPO) ማቅረብ የሚችል።

6. አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች የውል ማስከበሪ 10% ማሲዝ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

7. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት (10) አስር ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 ብር /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

9. ከጥቃቅን እና አነስተኛ ወይንም ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ ምን ዓይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸው ፍቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ካልሆነ ግን እንደ ማንኛውም ተጫራቾች ሰነድ በመግዛት እና የጨረታ ማስከበሪያ፣የውል ማስከበሪ በማሲያዝ መወዳደር ይችላሉ።

10. የጨረታው አሸነፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

11. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መሙላት እና በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው።

12. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ጽ/ቤት 700ሜ ገባ ብሎ ገላን ጉራ ቁ-1 የመ/ደ/ት/ቤት ስልክ ቁጥር 0913284601/ 0937751312

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

በወረዳ 10 የገላን ጉራ ቅድመ-መጀመሪያ፣ መጀመሪያ እና መካከለኛ  ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-12 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የገላን ጉራ ቅድመ መጀመሪያ እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T12:18:26.000Z
← Back to all tenders