Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል ዕቃዎችን በብሔረዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ካላቸው ተጫራቾች በብሔረዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፦ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ጋር

  • በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ አግባብነት ያለው ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው
  • በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገበ ሠርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው
  • የግብር ከፋይነት ቲን ነምበር ማቅረብ አለባቸው፡-
  • ከግብር ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸው ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡-
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ማቅረብ አለባቸው
  • ከሎት 01እስከ ሎት 10 ያሉትን የጨረታ ማከበሪያ ማቅረብ አለበት
  • የተጠየቁትን ስፔስፍኬሽን በትክክል የሚያሟላ እና በተጠየቀው መጠን ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆነ
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጤ/ሳ/ኮ/ን/እ/መ/መ/ሆል ግዥና ውል አስተዳደር የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሠዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡

1, የጨረታ ሰነዶቹ

  • ሎት 1- መድሃኒት 
  • ሎት 2 የላብራቶሪ ሪኤጀንት እና የህክምና መገልገያ ግብአት 
  • ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች 
  • ሎት 4 የህሙማን የምግብ አቅርቦት
  • ሎት 5 የሆስፒታሉ ሰራተኞች /ባለሙያዎች ካፍቴሪያ
  • ሎት 6 የሆስፒታሉ የህሙማን እና አስታማሚዎች ካፍቴሪያ
  • ሎት 7 የውሃ ቦቲ የመኪና ኪራይ
  • ሎት 8 የጭነት የመኪና ኪራይ
  • ሎት 9 የህክምና መገልገያ እና መለዋወጫ ዕቃዎች

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሁሉም ሎቶች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ወይም ባንክ ጋራንቲ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጤ/ሳ/ኮ/ን/እ/መ/መ/ሆ/ል ስም አዘጋጅተው ለብቻው በፖስታ በማሸግ ከኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ጨረታውን ዩኒቨርሲቲ ጤ/ሳ/ኮ/ን/እ/መ/መ/ሆል ባቀረበው ናሙና መሠረት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ውድድሮች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ለክፍሉ ማቅረብ ይኖርባዋል፡፡

4. በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር የተገለጹ የማቅረቢያ ጊዜ በሰነዱ ላይ የተገለጸ ሲሆን አሸናፊ ተጫራች ያሸነፏቸውን በሆሳዕና ከተማ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጤ/ሳ/ኮ/ን/እ/መ/መ/ሆ/ል ግቢ ውስጥ በሚገኘው መጋዘን በራሱ ትራንስፖርት አቅርቦ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ አድርገው በተሰጠው ስፔስፊኬሽን ላይ በመሙላትና የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ በማሳረፍ 1 (አንድ) ኦርጅናልና 2 (ሁለት) ኮፒ በማድረግ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጤ/ሳ/ኮ/ን/እ/መ/መ/ሆ/ል ግዥና ን/አስ/ር ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 4/1/2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው በ4/1/2019 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

7. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና (ውል ማስከበሪያ) የሚቆይ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ አሸናፊው በዕጣ የሚለይ ይሆናል፡፡

10. የጨረታው ውጤት ጨረታው ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ በፋክስ/በስልክ እና በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፣

11. ማንኛውም ተጫራች በውል ውስጥ የተካተቱትን ህጎች የማክበር ግዴታ አለበት፡፡

12.ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጤ/ሳ/ኮ/ን/እ/መ/መ/ሆ/ል የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 0461780711/0937733995 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡

ዋቸሞ ዩኒቭርሲቲ ጤ/ሳ/ኮ/ን/ኢ/መ/መ/ሆ/ል 


Tender details

  • Deadline: 2026-09-14
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-09-14 14:30
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Wachemo University Medical and Health Science College
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T12:33:38.000Z
← Back to all tenders