Vehicle (garage service)

ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት የመኪና ጥገና ጋራዥ አገልግሎት በግልፅ የጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የመኪና ጥገና /ጋራዥ/ አገልግሎት ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት የመኪና ጥገና ጋራዥ አገልግሎት በግልፅ የጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ እየገለጽን፡-

1. ተወዳዳሪዎች በጨረታ ለመወዳደር የሚችሉ ለመሆናቸው የንግድ ፈቃድ፤ የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፍኬትና የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2.ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ህጋዊ አካል ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የተፃፈ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3.ተጫራቾች ከዚህ ቀደም ከሠሩባቸው መ/ቤቶች ለሠሩበት ምስክርነት የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃዎችን

4.ተጫራቾች ጨረታውን 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

5.ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ለመወዳደር የሚያስችል ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6.ፋይናንሻል እና ቴክኒካል በኦርጂናል እና በኮፒ እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማሳረፍና በፖስታ በማሸግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ዋናው መ/ቤት አ.አ 7ኛ ፎቅ ማስገባት አለባቸው፡፡

7.አሸናፊው ድርጅት በአምስት ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር መቶኛ) የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የስምምነቱን ውል መፈረም አለበት፡፡

8.የጨረታ መዝጊያው ሰዓት ከደረሰ እና የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም

9.ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡

10.ጨረታው ኢአ መስቀል አደባባይ ፊንፊኔ ህንፃ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፋይ/ግዢ ንብ/አስ/መምሪያ 7ኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል፡፡

11.ጨረታው በሚከፈትበት ቀን \ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡

12. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ ይከፈታል፡፡

13.የጨረታ መዝጊያው ሰዓት ከደረሰ እና የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀረቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

14.ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-

ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፡- መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 011 552 10 09 /011 552 14 58/ ፖ.ሣ.ቁ. 9515 ፋክስ 011 551 3654

ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-16 14:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Wendo Trade and Investment Company
  • Buyer address: መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛ ፎቅ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T12:36:17.000Z
← Back to all tenders