Stationery
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ በወረዳ 08 ውስጥ የሚገኘው ሙሴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የፕላንት ማሽነሪ ጥገና /የተለያዩ/ እና ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2019ዓ/ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ በወረዳ 08 ውስጥ የሚገኘው ሙሴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019ዓ/ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች መሳተፍ ትችላላችሁ።
1. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የፕላንት ማሽነሪ ጥገና /የተለያዩ / እና ህትመት
ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ እና በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ማቅረብ የሚችሉ
2. ቲን ሰርትፊኬት /TIN/ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
3. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ከግብር ሰብሳቢው አካል የተሰጠ ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
4. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርትፊኬት
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር /በመክፈል ከት/ቤቱ ገንዘብ ቤት መውሰድ ትችላላችሁ
6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000/አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ/CPO/ማስያዝ ይኖርባቸዋል
7. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው
8. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት 7 የቅሬታ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ ከት/ቤቱ ጋር ውል በመዋዋል በዐ ቀናት ውስጥ እቃውን በራሱ ወጭ በራሱ መኪና አጓጉዞ ማቅረብ አለበት።
9. የገዛችሁትን የጨረታ ሰነድ ምንም ሳይቀነስ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ በሁለት ኤንቨሎፕ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10/ አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ። በመጨረሻው 10ኛው ቀን በ 11፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
10. አሸናፊ የሆነው ተጫራች /ድርጅት/የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10/ከ100/አስር ከመቶ/ያሸነፈበትን እቃ ዋጋ በCPO በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር ውል ይፈርማል
11.ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
አድራሻ ፡- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ ከንፋስ ስልክ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት
ወደ ሃኪም ማሞ ቤት በሚወስደው መንገድ ጫፍ ላይ ስልክ ቁጥር ፡- 011 442 4694/ 011 470 7199
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን በ 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-14 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Muse Elementary School
- Buyer address: ጎተራ ማሳለጫ ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ ከንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ወደ ሃኪም ማሞ ቤት በሚወስደው መንገድ ጫፍ ላይ
- Bid bond: 5000 (አምስት ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
- Posted at: 2026-09-01T12:53:01.000Z