Stationery

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በወረዳ 12 ስር በመጋቢት 28 ቅድ/አ/አ/መካ/ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚዉሉ እቃዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡ መጋቢት 28 ቅድ/አ/አ/መካ/ደ/ት/ቤት/01/2019

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በወረዳ 12 ስር በመጋቢት 28 ቅድ/አ/አ/መካ/ደ/ት/ ቤት በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚዉሉ

  • ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000
  • ሎት 2 የአይሲቲ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4,000
  • ሎት 3 የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000
  • ሎት 4 የደንብ ልብስ  የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000
  • ሎት 5 የእስፖርት ትጥቅ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,000
  • ሎት 6 የጥገና ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,000
  • ሎት 7 ቋሚ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7,000

ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

በዚህም መሰረት፡-

1. በጨረታው ለመወዳር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች ለእንያንዳንዱ ሎት የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታዉ ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መጋቢት 28 ቅድ/አ/አ/መካ/ደ/ት/ቤት⁄ የቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኮፒና ኦርጅናሉን በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1፣ ሎት 3፣ ሎት 4፣ ሎት 5፣ ሎት 6 እና ሎት 7 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 2 በቀረበው የፍላጎት መግለጫ /Specification/ መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።

8. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።

9 አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፅመው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ ማብራሪያ ወይም ጥያቄ
አድራሻ ፡ ሳሪስ በዳማ ሆቴል 58 ታክሲ ማዞሪያ ግንቦት 20 ት/ቤት
አጠገብ
የመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር: 011 419 1533
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በወረዳ 12 የመጋቢት 28 ቅድ/አ/አ/መካ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-09-14 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በ11ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nifas Slik/Lafto Sub City Megabit 28 Elementary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T13:05:14.000Z
← Back to all tenders