Stationery
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የእስቴሽነሪ እና የጽዳት እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesCleaning and Janitorial Equipment and Service
Central Ethiopia
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2019 ዓ/ም
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- የእስቴሽነሪ እና
- የጽዳት እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።
በዚህም መሰረት ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የTIN NO ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እንዲሁም የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆኑን
- የሚገልጽ ታከስ ክሊራንስ ያላቸው እና Online የአቅራቢነት ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖራባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ቡታጅራ ከተማ አስ/ፋ/ጽ/ቤት ግዢ ክፍል ቀርበው መግዛት ይችላሉ ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በህጋዊ ባንክ በተረጋገጠ CPO ለግዥው ብር 60,000/ሰላሳ ሺህ ብር ከሚያቀርቡት የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር በተናጠል ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖርየለበትም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ ቴከኒካል መረጃዎችን በአንድ ኤንቨሎፕ ፖስታ በማሸግ ማለትም 1 ኦርጅናል እና 2 ኮፒ በመለያየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዢ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ይህ ጨረታ አየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን በ04፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት 05፡00 ሰዓት ላይ ቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ላይ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም ።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል ።
- ይህ የጨረታ ዋጋ ለ45 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ ፡ - በስልክ ቁጥር 046-145–67-77 ወይም 046-115-06-07 ደውሎ መጠየቅ ይችላል
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-12 11:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ5፡00 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Butajira City Administration FEDB
- Bid bond: 60,000 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
- Posted at: 2026-09-01T13:24:52.000Z