Stationery
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 የአፍሪካ ብርሃን ቅድመ መደበኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት አመት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 የአፍሪካ ብርሃን ቅድመ መደበኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት 2019 ዓ.ም በጀት አመት 1ኛ ዙር ጨረታ የሚያስፈልጉት
- ሎት 1 6212 የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 2 6211 የደንብ ልብስ
- ሎት 3 6218 የአላቂ እቃዎች እና አቅርቦቶች
- ሎት 4 6215 አላቂ የትምህርት እቃዎች
- ሎት 5 6313 ፕላንት ማሽነሪ እና መሳሪያ መግዣ
- ሎት 6 6314 ለህንጻ ተገጣጣሚዎች
- ሎት 7 6243 ፕላንት ማሸነሪ እና መሳሪያ ጥገና
- ሎት 8 6219 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ለህንፃ ለቁሳቁስ ተገጣጣሚዎች እድሳት ጥገና በግልጽ ጨረታ መግዛት ስለፈለግን ብቁ አቅራቢዎች እንድትወዳደሩ እንጠይቃለን፡፡
1. ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በገንዘብ ሚ/ር እቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይ ከሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን በየሎቱ ማለትም ሎት 1 6212 ብር 4500 ሎት 2 6211 ብር 12000 ሎት 3 6218 ብር 8000 ሎት 4 6215 ብር 350 ሎት 5 6313 ብር 15000 ሎት 6 6314 ብር 8000 ሎት 7 6243 ብር 300 ሎት 8 6219 ብር 1500 በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ሊስት (ሲፒኦ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀ ሰነድ ከት/ቤቱ ሂሳብ ክፍል የማይመለስ ብር 200 (ሁለት) መቶ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በትምህርት ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ ዋናውንና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5.ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ዝርዝር ት/ቤቱ እስከ 25% መጨመር ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
6. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የአላቂ እቃዎችን ናሙና እና የቋሚ እቃዎች የተሟላ እስፔስፊኬሽን(በፎቶ) ከመወዳደሪያ የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
8, ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ10ኛው ቀን በ10፡00 ተዘግቶ በ10፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
9. የጨረታው አሸናፊ የአቃውን 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
10. ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት በጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ነው፡፡
11. አሸናፊው እቃውን ከማስገባቱ በፊት ከት/ቤቱ ጋር ውል መፈፀም ይኖርበታል፡፡
12. አሸናፊው ት/ቤቱ ባቀረበው መጠን ብዛት እቃዎችን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
13. ት/ቤቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሙሉ በሙሉ ካልተገኙ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
4. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. አሸናፊ ድርጅት ውል ከፈረመ በኋላ በጨረታ ሰነዱ በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ ካልቻለ እና ያሸነፈው እቃ በ10 (በአስር ቀን) ውስጥ ማቅረብ ካልቻለ ያስያዙትን ሲፒኦ በመውረስ በት/ቤቱ ፋይናንስ ገቢ በማድረግ ለሚመለከተው አካል የጥፋተኝነት ደብዳቤ የምንፅፍ መሆኑን እናሳውቃለን።
16. በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅታችሁ ያላችሁ ተጫራቾች ሰነድ ልትገዙ በምትመጡበት ጊዜ አምራች መሆናችሁን የሚገልፅ ደብዳቤ እና ንግድ ፍቃዳችሁን ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
17. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ቫት ተደምሮ መቅረብ አለበት፡፡
አድራሻ ፡- ከአብነት ወደ ጦርሀይሎች በሚወስደው መንገድ ኮካ ፋብሪካ ሳይደርስ ወደ አማኑኤል በሚወስደው መንገድ ቅዱስ አማኑኤል ህንጻ ፊት ለፊት ነው::
ስልክ ቁጥር 0118279312
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 የአፍሪካ ብርሃን ቅድመ መደበኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ10፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-12 16:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ10፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Africa Birhan Kindergarten and Primary School
- Buyer address: ከአብነት ወደ ጦርሀይሎች በሚወስደው መንገድ ኮካ ፋብሪካ ሳይደርስ ወደ አማኑኤል በሚወስደው መንገድ ቅዱስ አማኑኤል ህንፃ ፊት ለፊት ነው
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
- Posted at: 2026-09-01T13:25:23.000Z