Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የቅምብቢት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አንደኛ ዙር ግዥ በቅምብቢት ወረዳ ስር ላሉ ባለ በጀት መ/ቤቶች የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ እና ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪናና የሞተር ጎማዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የቅምብቢት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አንደኛ ዙር ግዥ በቅምብቢት ወረዳ ስር ላሉ ባለ በጀት መ/ቤቶች የተለያዩ፡-

  • የጽህፈት መሳሪያ እና ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • የጽዳት እቃዎች
  • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • የመኪናና የሞተር ጎማዎች
  • የደንብ ልብስ
  • የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በየስራ ዘርፉ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAI 15% ተመዝጋቢ የሆናችሁ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላችሁ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል። 11ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ካላንደር የሚዘጋው ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን የሚከፈት ይሆናል። የጨረታውን ሰነድ በቅምብቢት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ዝርዝር መጠይቆችን የያዘውን ሰነድ በማይመለስ በብር 1000 በካሽ መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በካሽ ወይም ሲፒኦ “CPO” ማስያዝ አለባቸው።

ተጫራቾች በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ውሉን ፈጽሞ እቃዎችን የማስገባት ግዴታ አለበት።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 78 ኪሎ ሜትር ሸኖ ከተማ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910 913798 በመደወል ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የቅምብቢት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-12 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: North Shewa Zone Kembebit Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Buyer address: ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 78 ኪሎ ሜትር ሸኖ ከተማ
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T13:50:36.000Z
← Back to all tenders