Materials

የድል በር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019

በጉለሌ ክ/ከ ት/ት/ጽ/ቤት ድል በር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመደበኛ በጀትና በውስጥ ገቢ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ የሚከተሉትን መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት - 1 ለጽህፈትና የትምህርት መሳሪያዎች - 12,000.00 (አስራ ሁለት ሺ ብር)
  • ሎት - 2 የደንብ ልብስ ግዥ- 17,000.00 (አስራ ሰባት ሺ ብር)
  • ሎት- 3 የፅዳት እቃዎች 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር)
  • ሎት- 4 የኤሌክትሪክና የውሃ እቃዎች 2,000.00 (ሁለት ሺ ብር)
  • ሎት- 5 ቋሚ ዕቃ ኤሌክትሮኒክስ - 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • ሎት-6 የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት - 1,000.00 (አንድ ሺ ብር)
  • ሎት-7 የት/ቤቱ ክበብ የመምህራ የሰራተኞች እና የተማሪ ክበብ ለማከራየት-7000.00 (ሰባት ሺ ብር)
  • ሎት-8 የተለያዩ ሪፈርንስ የያዙ መፅሓፍቶች - 1,500.00 (አንድ ሺ አምስት መቶ ብር)
  • ሎት-9 የላብራቶሪ ዕቃዎች 1,500.00 (አንድ ሺ አምስት መቶ ብር)
  • ሎት- 10 የመኪና ትራንስፖርት አገልግሎት- 5,000.00 (አምስት ሺ ብር)
  • ሎት- 11 የጉልበት እና ጭነት አገልግሎት- 2000.00 (ሁለት ሺ ብር)
  • ሎት- 12 ህትመት- 1,500.00 (አንድ ሺ አምስት መቶ ብር)
  • ሎት- 13 የፕላንትና ማሽነሪ ጥገና አገልግሎት- 1,000.00 (አንድ ሺ ብር)
  • ሎት 14 ቦረንዳዩ በር፣ መስታወት፣ ኮርኒስ እና ቀለም ቅብ ጥገና አገልግሎት 2,000.00 (ሁለት ሺ ብር)

በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በማስያዝ መሳተፍ የሚትችሉ ሲሆን፤

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል,

3. ተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል

4. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

5. በሁለትና ከዛ በላይ ሎት ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ለእያንዳንዱ ሎት የተሟላ ማስረጃ በማያያዝ በተለያዬ ፖስታ በማሸግ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የተሟላ ማስረጃ የሌለው ሎት ውድቅ ይሆናል።

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።

7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ከትቤቱ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 በሎት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ።

8. በመንግስት የተደራጁ ልዩ አስተያዬት የሚደረግላቸው ድርጅቶች በድጋፍ ደብዳቤ መሳተፍ የሚችሉት እራሳቸዉ ባመረቱትና እሴት በጨመሩበት እቃዎች ላይ ብቻ ነው።

9. ት/ቤቱ ከሚገዛው ዕቃ ግዢ ላይ ከውል በፊት 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።

10. አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለበት።

11. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ እስከ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማድረስ አለበት።

12. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በወሰዱት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ዋጋውን በመሙላት የግዢውን አይነትና የድርጅቱን ሙሉ ማስረጃ የታሸገው ፖስታ ላይ በመጻፍ ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታ ላይ የድርጅት ማህተምና ፊርማ በማስቀመጥ ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

13. ለሚያቀርቡት ዕቃዎች ፖስታውን ሲያስገቡ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙናዎች መግባት አለባቸው።

14. ትምህርት ቤቱ ካስቀመጠው ተፈላጊነት /specification/ አንሰው ወይም በልጠው የሚመጡ ናሙናዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

15. የትምህርት ቤቱን የጨረታ መመሪያ ክብ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ከፖስታው ጋር ማስገባት አለባችሁ።

16. ጨረታው በ10ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።

17. ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት የሸነፈውን ጠቅላላ የዕቃውን መጠን 25% እስከ 6 ወር ድረስ ተጨማሪ ቢጠየቅ በራሱ ዋጋ የሚያቀርብ ይሆናል።

18. ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ድልበር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከሰሜን ማዘጋጃ ከፍ ብሎ ሴንቲሜሪ ት/ቤት ጎን ስልክ ቁጥር 011 157 0942

የድል በር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-14 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Dil Ber Secondary School
  • Buyer address: ሰሜን ማዘጋጃ ከፍ ብሎ ሴንቲሜሪ ት/ቤት ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በሎት 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T13:53:40.000Z
← Back to all tenders