Construction Machinery

ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ክሬሸር ፕላንት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት (መከራየት) ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ዝርዝር መረጃ

ድርጅታችን ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በደቡብ ምዕራብ ኢ/ያ ሸካ ዞን ያኪ ወረዳ ሺሺንዳ ቴፒ መንገድ ስራ ፕሮጀክት ሊሰራ የሚችል ክሬሸር ፕላንት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት (መከራየት) ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ልታሟሏቸው የሚገባችሁ ዝርዝር ሁኔታዎች፦

1. የማሽኑ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር (ሊብሬ)

2. ተጫራቾች የ2019 ዓ/ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርቲፊኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ

3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀ ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ከ 27/12/2018 ዓ/ም ጀምሮ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) እየከፈሉ በአዲስ አበባ ቦሌ ሜጋ ህንፃ አጠገብ ከሚገኘው ዋና መስሪያቤታችን ቢሮ ቁጥር 1502 ወይም በመቀሌ ላጪ ከሚገኘው ቅርንጫፍ መስሪያቤታችን ኢኩፕመንት አስተዳደር መምሪያ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ከድርጅታችን የተሰጣቸው ኦርጅናል ፎርም/ቅፅ ብቻ ተጠቅመው ያለ ስርዝ ድልዝ ቫት ሳይጨምር (ከቫት በፊት) ነጠላ ዋጋ ሞልተው ፈርመው እና ማህተም አድርገው በታሸገ ኢንቨሎፕ እንዲልኩልን ወይም ጨረታው በሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት በአካል ይዘው እንዲመጡ

5. ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) ሲፒኦ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

6. ለድርጅታችን ስራ የሚውል የነዳጅ ወጪው በድርጅታችን የሚሸፈን ይሆናል።

7. የማሽኑ የመጓጓዣ ፣ የተከላ፣ የመመለሻ እና ሌሎች ወጪዎች (ዋጋ) በሙሉ በአከራይ (በደንበኛ) የሚሸፈን ይሆናል።

8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኞ 04/01/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት አዲስ አበባ በሚገኘው የድርጅታችን ዋና መስሪያቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1601 እንዲሁም በመቀሌ ላጪ በሚገኘው ቅርንጫፍ መስሪያቤታችን 4ኛ ፎቅ ሁኖ ጨረታው ሲከፈት የተገኘም ሆነ ያልተገኘ ደንበኛ በውጤቱ ተገዢ ይሆናል።

9. ጨረታው ያሸነፈው ተወዳዳሪ/ተጫራች ማሽኑ ሊያቀርብ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ በአምስት ቀን ውስጥ መጓጓዝ የሚጀምርና በአንድ ወር ውስጥ ለመጓጓዣና ለተከላው የሚያስፈልጉ እንደ ክሬንና ሌሎች ኢኩፕመንቶች በራሱ ወጪ ሸፍኖ የማሽን ተከላውን ጨርሶ ለስራ ዝግጁ የማድረግ ግዴታ አለበት። ጨረታውን ያሸነፈው ደንበኛ/ተጫራች ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ የሚፈለገው የክሬሸሩ ተከላውን ጨርሶ ለስራ ዝግጁ ካላደረገ (ካልቻለ) እሱ ባሸነፈው ዋጋ ሌሎች ደንበኞች ወይም አቅራቢዎች ሊያቀርቡ ይችላሉ።

 10. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 09 91 19 04 34/ 09 14 02 61 07 ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ። የክሬሸር ፕላን የጨረታ ዋጋ መሙያ ቅፅ 

የስራ ፕሮጀክት ሺሺንዳ ቴፒ መንገድ ስራ ፕሮጀክት

የማሽን ዓይነት

 

የማሽኑ አቅም ካፓሲቲ

 

ማሽኑ የተሰራበት ዘመን

 

የስራ መለኪያ

 

የሚፈጭ ዓይነት ጠጠር ብዛት በሜ3

 

የአንድ ሜትር ኪዩብ (M3) ዋጋ በብር ከቫት በፊት

ክሬሸር ፕላንት

 

200 TPH ሆኖ (ቢያንስ 60ሜ3 በሰዓት እና 6003 በቀን ጠጠር የሚፈጭ/የሚ ያመርት)

 

 

በሜትር ኪዩቢክ (M3)

 

1.Asphalt aggregate

 

1.1 G4 = 4393.21 M3

 

1.2 G3=8634.93  M3

 

1.3 G2 = 5605.13 M3

 

1.4 G1 = 11664.73 M3

 

2.Base-coarse aggregate.

 

2.1 Base-coarse aggregate 69,850.70 M3

 

3.Concrete aggregate

 

3.1 G4 = 43964 M3

 

3.2 G3 = 10991 M3

 

4.Crushed sand

 

4.1 Crushed Sand 65,000 M3

 

ድምር

220,103.70 M3

 

ማብራሪያ፡ በቅፁ የሚሞላ ዋጋ የቫትና የነዳጅ አይጨምርም።

ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-09-14
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Bid opening: 2026-09-14 10:30
  • Bid opening (note): ሰኞ 04/01/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Sur Construction PLC
  • Buyer address: ከደምበል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ሜጋ ህንፃ አጠገብ
  • Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T14:24:00.000Z
← Back to all tenders