Building Construction
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የአንድ ማዕከልና የላንድስኬፕ ስራ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የአንድ ማዕከልና የላንድስኬፕ ስራ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
1. ደረጃቸው GC- 5/BC 5 ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተቋራጮች 2018 ዓ.ም ፍቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ወይም ከሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።
2. አስፈላጊ የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሳሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው።
3. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሰሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሰሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ወደ ስራ ገብተው ያላስተካከሉ ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።
4. የሥራ ተቋራጮች ለውድድር የቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦርጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
5. የጨረታ ማስከበሪያ (Bic security) 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /Bank GAURANIE ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
6. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፍቃዳቸውን እና ተ.ዕ.ታ(VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ25 (ሃያ አምስት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000347602028 በማስገባት እስሊፕ ይዞ ሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 230 ሰነዱን መወሰድ ይችላሉ።
7. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታውን ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
8. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/ security) ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ (ኮፒ) እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል)እና ሁለት ቅጂ (ኮፒ) ሰነዶችን በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከትተው በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ26ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰአት ላይ ይከፈታል፤ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግድም።
10. አሰሪው መሥሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
11. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0462125584 ወይም 0913175091
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሀዋሳ
Tender details
- Deadline: 2026-09-26
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ26ኛ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-26 14:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ26ኛ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama National Regional State Supreme Court
- Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
- Posted at: 2026-09-01T15:08:17.000Z