Stationery

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 13 ገርጂ ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019

በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ13 ገርጂ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎት 1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ ሎት 2.አላቂ የጽዳት እቃዎች ፣ ሎት 3 የደንብ ልብሶች፣ሎት 4. የህትመት ስራዎች ሎት 5. ቋሚ እቃዎች ኤሌክትሮኒክስ፣ የእንጨትና ብረት ስራዎች እና የመኪና ጎማ ሎት 6.ህንጻ መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት7.አላቂ የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች 8.የጭነት መኪና ኪራይ አገልግሎት እና 9. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የላውንደሪ ማሽን የጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለ መክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው

4. ከሎት 8 (የጭነት መኪና ኪራይ አገልግሎት) በስተቀር ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

5. በሎት 8 የጭነት አገልግሎት ተወዳደሪ የመኪና ሊብሬ፣የንግድ መለያ ቁጥር /TIN/ ሰርተፍኬት፣ የበጀት ዓመት ግብር የከፈሉበት እና መንጃ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል።

6. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው።

ሎት ቁጥር

 

የሎት ዝርዝር

 

የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር

ሎት1

አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች

4000ብር

ሎት 2

አላቂ የጽዳት እቃዎች

5500ብር

ሎት 3

የደንብ ልብሶች

5000ብር

ሎት 4

የህትመት ስራዎች

4000ብር

ሎት 5

 

ቋሚ እቃዎች ኤልክትሮኒክስ፣ የእንጨትና ብረት ስራዎች እና የመኪና ጎማ

6000ብር

ሎት 6

ህንጻ መሳሪያ እቃዎች

3500ብር

ሎት 7

አላቂ የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች

7000ብር

ሎት 8

የጭነት መኪና ኪራይ አገልግሎት

2000ብር

ሎት 9

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የላውንደሪ ማሽን የጥገና

2500ብር

7. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 401 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል።

8. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10/አስር/ተከታታይ የሥራ ቀናት 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 410 በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

9. ጨረታው በ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ታሽጎ በነጋታው ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

10.ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ማስያዝ አለባቸው።

11. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።

12. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት መስሪያ ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

13. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20 ፐርሰንት የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ለጨረታው የሰጡት ዋጋ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

አድራሻ፡-ወረዳ 13 ገርጂ ጤና ጣቢያ ከገርጂ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን 200 ሜ ወረድ ብሎ ስልክ ቁጥር፡ 011-865-0287

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክፍለ  ከተማ አስተዳደር
ወረዳ 13 ገርጂ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-14 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ታሽጎ በነጋታው ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bole Sub City Woreda 13 Gerji Health Post
  • Buyer address: ወረዳ 13 ገርጂ ጤና ጣቢያ ከገርጂ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ 400 (አራት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T15:12:15.000Z
← Back to all tenders