Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል የፅዳት እና የፅህፈት እቃ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ጠ/ሆስፒታል 0001/19
የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት ለ ሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን ግዢን
- ሎት - 1-የፅዳት አቅርቦት
- ሎት - 2- የፅህፈት እቃ አቅርቦት ከሚያሟሉ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ የግዢ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጹትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ ለ 2019 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- የንግድ ዋና ምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ / ቫት/ ተመዝጋቢ የሆነ ለዚህም የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ ፣
- የታክስ መለያ ቁጥር /ቲን/ የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ፣
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ ፣
- ተወዳዳሪዎች ከዝህ በፊት በየሰሩበት የመልካም ስራ አፈፃፀም ምስክር ወረቀት የሚያቀርብ
የጨረታ ማስከበሪያ ብር - ለ ሎት - 1 ብር - 5,000 /አምስት ሺ ብር ብቻ/
- ለ ሎት - 2 -ብር 5,000.00 /አምስት ሺ ብር ብቻ/
ከዚህ በላይ የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች ይህ ማስታወቂያ መልከተ ድሬ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላል፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ መልክተ ድሬ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 /አስራ አምስት / ተከታታይ የስራ ቀናት የአየር ላይ ቆይታ በኋላ በ 16 ኛው ቀን ከጥዋቱ 3:30 ላይ የጨረታ ሰነድ መቀበያ ሳጥኑ ተዘግቶ ታሽጎ በዚያኑ እለት ከቀኑ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
ተጫራቾች አሸናፊ የሆነበትን እቃዎች በራሱ የትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎችን በራሱ በመሸፈን ሆስፒታሉ በሚፈልግበት ቦታ የማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ ማብራሪያ ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 3 ወይም በስልክ ቁጥር 0225 -1124968 ላይ በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ መልከተ ድሬ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3:30
- Bid opening: 2026-09-12 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ መልከተ ድሬ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4:30
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: Sabiyan General Hospital
- Bid bond: በየሎቱ 5,000 (አምስት ሺ ብር)
- Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር)
- Published on: Melekite Dire (Aug 26, 2026)
- Posted at: 2026-09-02T06:31:51.000Z