Equipment and Accessories

ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በ2019 በጀት ዓመት የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሎች፣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ካሜራና የካሜራ አክሰሰሪዎችን እንዲሁም የካፍቴሪያ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በ2019 በጀት ዓመት ኮርፖሬሽኑ ለሥራ የሚፈልጋቸውን ከዚህ ቀጥሎ በሎት የተለዩ ዕቃዎችን

  • ሎት 1 የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሎች
  • ሎት 2 የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • ሎት 3 ካሜራና የካሜራ አክሰሰሪዎችን
  • ሎት 4 የካፍቴሪያ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. በመሆኑም በዚህ ጨረታ

  • በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
  • የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍከት ያላቸው
  • የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው ድርጅቶች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

2. ኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ካሜራና የካሜራ አክሰሰሪዎችንና የካፍቴሪያ ቁሳቁሶችን ዝርዝር የሚገልጽ ጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብቻ/ በመክፈል ሀዋሳ ወንዶ ንግድ ኩባንያ ህንጻ ጀርባ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 በአካል ቀርበው መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ 20,000/ሃያ ሺህ/ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ CPO ግዥውን በሚፈጽመው ድርጅት ስም አዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርበታል። ከተጠየቀው ውጪ የሚቀርብ ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም።

4. ተጫራቾች አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው።

5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውንና ፈርማቸውን አሟልተው የእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።

6. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ኮርፖሬሽኑ ለጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል።

7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462121480/0916037261 ደውሎ  መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
የሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-14
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ
  • Bid opening: 2026-09-14 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Sidama Broadcasting Corporation
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ 20,000 (ሀያ ሺህ ብር)
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
  • Posted at: 2026-09-02T07:52:40.000Z
← Back to all tenders