Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልፅ የጨረታ ግዥ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም 1. የደንብ ልብስ 2. አላቂ የፅዳት እቃዎች 3. አላቂ የፅህፈት መሳሪያ 4. የኤልክትሮኒክስ እና የፈርኒቸር እቃዎች 6. የህዝብ ትራንስፖርት 7. የመስተንግዶ 8. የህትመት ውጤቶች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ፍቃድ ያላችው እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
4. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በፖስታ ማቅረብ የሚችል
ሌሎቶች የተቀመጠው በኢትዮጵያ ብር
ሎት 1 ደንብ ልብስ 13000
ሎት 2 አላቂ የፅዳት እቃዎች 12000
3. ሎት 3 አላቂ የፅህፈት መሳሪያ 13000
4. ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር እቃዎች 10000
5. ሎት 5 የህዝብ ትራንስፖርት 7000
6. ሎት 6 መስተንግዶ 9000
7 ሎት 7 . የህትመት ውጤቶች 1200
8. ሎት 8. የዘር ግዥ 400
5. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ በተቋሙ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 በአካል እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
7. ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡30 ታሽጎ በማግስቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
8. ተጫራቾች ያሸነፉበትን የውል ማስከበሪያ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡
9. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው መቅረብ የማይችሉትን ቋሚ እቃዎች መ/ቤቱ ባቀረበው ናሙና መሰረት በአካል ማሳየት የግዴታ ነው፡፡
10. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ እና ውል በተሰጣቸው 5 ቀን ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት ለፅ/ቤቱ ማስረከብ አለበት፡
11. መ/ቤቱ ጨረታ ሰነድ ላይ ካቀረበው እቃ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
13. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም አድራሻ ቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ገርጂ ናይጄሪያ ኢምባሲ አፖርትመንት አጠገብ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ወይም ገርጂ ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0118 721 213
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡30
- Bid opening: 2026-09-14 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ10ኛው ቀን በማግስቱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bole Sub City Woreda 14 Finance Economic Development Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
- Posted at: 2026-09-02T08:27:25.000Z