Stationery
የምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2019 ዓ/ም የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን አላቂ፣ ቋሚ እቃዎች፤ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለዞኑ ሴክቴር መ/ቤት ለመግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesOffice Machines and Accessories
Oromia
More tags
Computer and AccessoriesIT and TelecomEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsSpare Parts and Car Decoration MaterialsTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsOffice FurnitureFurniture and FurnishingAmharic2merkatoWest Wollega Zone FEDB
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2019 ዓ/ም
- የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን አላቂ፣
- ቋሚ እቃዎች፤
- የመኪና ጎማዎች እና
- የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለዞኑ ሴክቴር መ/ቤት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ እና በተወዳዳሪዎች መመሪያ ደንብ መሠረት ተጫራቾች ቀርበው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
- በመንግስት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ የምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ህጋዊ አካል ማቅረብ የሚችሉ፤
- የ2018 /2019 ዓ ም ግብር አጠናቀው የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡና ለታክስ ከፋይነት (TiN)
- የተመዘገቡና ተጨማሪ ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
- ለጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት ዋጋ 2% በተረጋገጠ (CPO) ከማስረጃቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጨራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር(500) አምሰት መቶ በመክፈል የግዥ ከፍል ከመ/ቤቱ (G+1) ምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ፅ/ቤት መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን ምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ፅ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዓይነት የቢሮ ዕቃ መሆኑን እንደዚሁም የድርጅቱን ስም
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ በኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- በሚያቀርቡት የተለያየ ፖስታ ላይ በኦሪጅናሉና በኮፒው ላይ በግልጽ በመጻፍ በድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ አስደግፈው ማቅረብ አለባቸው፤
- ተወዳዳሪዎች ናሙና እንዲቀርብባቸው የተጠየቁትን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ማቅረብና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ቆጥሮ ማስረከብ አለባቸው፡
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን፣ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 (በስምንት ሰዓት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሲሆኑ ዕቃዎቹን በራሳቸው ማጓጓዣ እስከ ገዥው ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው!
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0577712547 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታንው በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-19
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን፣ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-19 14:30
- Bid opening (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን፣ ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: West Wollega Zone FEDB
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
- Posted at: 2026-09-02T08:50:34.000Z