Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መሰተዳደር የመቱ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙት ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መሰተዳደር የመቱ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙት ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች ፣ የኤለክትሮኒክሰ ዕቃዎች፣ የፈርንቸር ዕቃዎች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ ሞተር ሳይክሎች እና የተለያዩ የመኪና እና ሞተር ሳይክሎች ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ።

.

ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ቀን

ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት

የዕቃው ዓይነት

የጨረታው ቁጥር

የጨረታው መክፈቻ ቀን ሰዓት

1

27/12/2018

14/1/2018

የጸህፈት መሣሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች

1

15/1/2019

2

14/1/2019

4:00

የፈርኒቸር ዕቃዎች

2

4:30

3

 

 

የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

3

 

4

 

 

የደንብ ልብስ ዕቃዎች

4

 

5

 

 

የመኪና ጎማዎች እና የሞተር ጎማዎች

5

 

6

 

 

ሞተሮች

6

 

የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

  • በዘርፉ የታደሰ የ2018 ወይም 2019 ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለዉ እና የዘመኑ ግብር የከፈለና ማሰረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ።
  • በንግድ ሚንሰተር በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  • ለጨረታ ማስከበሪያ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ)ብር በሲፒኦ (CPO)ማሰያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO)ማስያዝ የሚችል።
  • ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፉ በኃላ ለበጀት ዓመቱ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ የሆነና ዕቃዎቹን በራሱ ሙሉ ወጪ በታዘዘ ጊዜ ውስጥ እስከ ጽ/ቤቱ ለማቅረብና ቆጥሮ ለማሰረከብ ፈቃደኛ የሆነ፣
  • ተጫራቹ የዕቃዉን ሞደል ባልተገለፀበት ቦታ በጨረታው ዝርዝር ላይ መግለፅ አለበት።
  • ተጫራቹ የተፈለገዉን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  • ተጫራቹ ለሚያቀርባቸዉ የደንብ ልብሶች ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይኖረባቸዋል።
  • ጨረታው ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቆ በዚህዉ ቀን በ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል።
  • ተጫራቾች እያንዳዱን የጨረታዉን ሰነድ በማይመለሰ አንድ ሺህ ብር (1000ብር) ከመቱ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በመግዛት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መሰተዳደር ከመቱ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ቁጥር 6 የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ ሰነድ በመውሰድ የአንዱን ዋጋ በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ዉሰጥ ማሰገባት ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች በሌላ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው።
  • የሚወዳደሩበት ሰነድ ሰርዝ ድልዝ የሌለዉ እና የሚነበብ ሆን አለበት።
  • ተወዳደሪዎች ዋጋን የሚገልጽ ሰነድ ፣ ፍቃድንና የተለያዩ ተፈላጊ ሰነዶችን ለየብቻ ኦሪጀናል እና ኮፒ በፖሰታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  • መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0924 669 731

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር የመቱ ከተማ ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-25 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Metu City FEDB
  • Bid bond: 200,000.00 ብር
  • Bid document price: 1,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
  • Posted at: 2026-09-02T10:08:25.000Z
← Back to all tenders