Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የኮከበጽባህ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳድር ድጋፍ የስራ ሂደት ለ2019 ዓ.ም. ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውል ግበዓቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኮከበጽባህ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳድር ድጋፍ የስራ ሂደት ለ2019ዓ.ም ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውል ግበዓቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የምትጫረቱበትን እቃዎች በየሎታቸው ያስቀመጥን መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  • ሎት 1 የሰራተኛ የደንብ ልብስ................ብር 5000
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃ.............................ብር 5000
  • ሎት 3 የህትመት ሥራዎች........................ብር 1500
  • ሎት 4 አላቂ የትምህርት ዕቃ......................ብር 5000
  • ሎት 5 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች......................ብር 3000
  • ሎት 6 ለሕንጻ ተገጣጣሚዎች...................ብር 3000
  • ሎት 7 ልዩ ልዩ መሣሪያዎች........................ብር 5000
  • ሎት 8 ለማሽነሪ ኮምፒዩተር ፕሪንተር ላፕ ቶፕ...... ብር 5000
  • ሎት 9 ቋሚ የቢሮ ዕቃ ፈርኒቸር.........................ብር 5000

ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡

1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ

2. በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስተር በአገልግሎት አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ወይንም (supplier List) ያለው

3. የቫት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ /400/አራት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 7 መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. የውል ማስከበሪያ የሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ብር በቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ የማንቀበል መሆኑን እየገለጽን በባንክ በተረጋገጠው ሲፒኦ ማስገባት ይኖባቸዋል ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ የሆኑበትን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ በማስያዝ እና የግዥ ውል ስምምነት መፈፅም ይኖርባቸዋል፡፡

8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ኦርጅናልና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስክ 11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡

9. ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ውድድሩን አሸናፊ የሚሆኑ ድርጅቶች ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን ት/ቤቱ ድረስ በማምጣት ለንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸዉ፡፡

11. በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው የሚሠሩ ከሆነ እና ተጨማሪ እሴት አማራጮች ከሆኑ ካደራጀው አካል ደብዳቤ ይዘዉ መቅረብ አለባቸው፡፡

12. አድራሻ፡- ከራሺያ ኢንባሲ አጠገብ ወደ አራት ኪሎ ሲኬድ ቀበና ድልድይ አካባቢ ኮከበጽባህ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 011 666-28 26 / 011-663-00-1

ማሳሰቢያ ት/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

የኮከበጽባህ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-14
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-14 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kokebe Tsebah General Secondary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
  • Posted at: 2026-09-02T10:14:14.000Z
← Back to all tenders