Textile, Garment and Leather

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር AMFI 03/2019

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ምድብ 1፡ የሰራተኞች ደንብ ልብስ
  • ምድብ 2፦ የሶፍትዌር ዕቃዎች

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡

1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለምድብ 1 የሚቀርብ 80,000.00 (ሰማኒያ ሺህ ብር)እና ለምድብ 2 የሚቀርብ 100,000 /አንድ መቶ ሽህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በተከፈለበት በአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኢማ ደረሠኝ ወይም የባንክ ዋስትና እንደምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 (አሥራ አንድ ሰዓት) ድረስ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ለአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በአሐዱ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 0003230410101 ገቢ በማድረግ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ አቅርበው ከአኩፋዳ ማይከሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ወሰን ቅርንጫፍ መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዙ ሰነዶች የዋጋ ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን ሲሆን ለምድብ 1 ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ለምድብ 2 ከቀኑ 5፡30 /አምስት ሰዓት ተኩል/ ድረስ ብቻ ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ወሰን ቅርንጫፍ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ሲሆን ለምድብ 1 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከቀኑ 4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ላይ፡ ምድብ 2 ከረፋዱ 5፡30 /አምስት ተኩል/ ታሽጎ በእለቱ ከቀኑ 6፡00/ስድስት ሰዓት/ ላይ በግልጽ ተከፍቶ የእቃው ዋጋ ተጫራቾችና ታዛቢዎች ባሉበት ይነበባል። የመክፈቻ ቀኑ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም ብሔራዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል። /ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል/።

6. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው አግባብ በራሳቸው ሙሉ ወጪ አኩፋዳ ማይከሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ዋና መ/ቤት (ደብረ ብርሃን አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ሕንጻ) ድረስ አምጥተው ገቢ ማድረግ አለባቸው።

7. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።

8. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በተቋሙ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልፃለን።

9. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 637 6668/ 011 637 6457 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-12 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ/ማ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
  • Posted at: 2026-09-02T10:19:13.000Z
← Back to all tenders