Vehicle (garage service)

በቤንች ሸኮ ዞን በሼይ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ከነ ሰርቪስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ 

በደ/ቡ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በቤንች ሸኮ ዞን በሼይ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ከነ ሰርቪስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት በጨረታ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ፣ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣ በማቅረብ በሼ/ቤ/ወ/ ገ/ጽ/ቤት የጨረታው ሰነድ በማይመለስ 500 ብር/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. የታደስ የብቃት ማረጋገጫ በተገቢው ሁኔታ ማቅረብ የሚችል
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 ብር/ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዥ ይጠበቅበታል፡፡
  4. እያንዳንዱ ፖስታ በታሸገ ማህተም በመምታት በሙሉ አድራሻ በመጻፍ እና በመፈረም ኦርጅናል ኮፒ የሚል ጽሁፍ በግልጽ በሚታይ ቦታ መጻፍ አለበት፡፡
  5. ተጫራቹ ሁሉንም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች ህጋዊ ተወካይ ፊርማ እና እንዲሁም የደርጀቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  6. ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ስራ ቀናት ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለአንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. ጨረታ የሚታሸገው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን በሼ/ቤ/ ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ/ር 7 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካይ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. ጨረታው የሚከፈትበት ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው በሼ/ ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኘው ይከፈታል፡፡
  9. የሼ/ቤ/ወ/ ፋ/ጽ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት በህግ የተጠበቀ ነው።
  10. ጨረታው ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ለ30/ሰላሳ ቀናት/ ብቻ ይሆናል፡፡
  11. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሀሳብ እና ሌሎችም ተጨማሪ ማረጋገጫዎች የሚመለከተው ኃላፊ ፊርማና ማህተም ካልተደረገባቸው የቀረበው የመወዳደሪያ ሀሳብ ሊሰረዝ ይችላል፣
  12. ፅ/ቤታችን የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ከነ ሰርቪስ ለማስጠገን የሚፈፅመው የተዘረዘሩትን ሁኔታዎችና የቴክኒካል መመዘኛዎች ከሚያሟሉት መካከል በመንግስት በግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሠረት ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች የግዥ ትዕዛዝ በመስጠት ይሆናል፣
  13. የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15(አስራ አምስት ቀን) ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
  14. አድራሻ፡- በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ቤንች ሸኮ ዞን ሼይ ቤንች ወረዳ ፋይናስ ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር፡- 0952424403/0917972404

በቤንች ሸኮ ዞን የሼይ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-21 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው 4፡30 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Bench Maji Zone Shey Bench Woreda FEDB
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 03, 2026)
  • Posted at: 2026-09-03T08:22:43.000Z
← Back to all tenders