Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ያኢጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የመጀመሪያ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

መለያ ቁጥር 001/19

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ያኢጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሎት ዝርዝር

ሲፒኦ ማስያዣ 1%

ሎት 1 የደንብልብስ

6,000

ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃ

5,000

ሎት 3 የህትመት ስራዎች

500

ሎት 4 የመጀመሪያ ህክምና መስጫ መድኃኒት

2,000

ሎት 5 አላቂ የት/ ዕቃዎች

5,000

ሎት 6 በአላቂ የፅዳት ዕቃዎች

5,000

ሎት 7 ቋሚ እቃ

7,000

ሎት 8 ህንፃና ቁስቁስ ጥገና ለተገጣጣሚ እድሳት

4,000

ሎት 9 ለፕላንት ማሽነሪ ጥገና

2,000

1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3. በጨረታው የሚወዳደር የግዥው መጠን ከ100,000 በላይ ከሆነ የቫት ከፋይነት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

4. አነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ የራሳችሁን እሴት ያልጨመራችሁ እና አምራች ያልሆናችሁ እንደማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መወዳደር ትችላላችሁ።

5. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውን ከመጫረቻ ሰነድ ዋናው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ዕቃዎች ዝርዝር ከሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ያኢጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በመምጣት በአንድ ሎት 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) የማይመለስ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ በየሎቱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሆኖ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዋናውንና ቅጅውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ውስጥ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 (ለአስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ዋጋ በመሙላት ማስገባት አለባችሁ፡፡

10. በአስረኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

11. መስሪያ ቤቱ በሚገዛቸውአቃዎች ላይ 20% የመጨመርም የመቀነ ስም መብት አለው፡፡

12. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ቢሮ ቁ 3 በአካል በመገኘት ወይም በስልክቁ. 0913 397 864 / 0911 522 182 / 0972 266 675 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

13. ናሙና መቅረብ ባለበት ዕቃዎች ላይ ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡

14. አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ያኢጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ክፍል ማቅረብ አለባቸው፡፡

ማሳሰቢያ፦

መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ መድሃኒዓለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ባለው ኮብልስቶን 30 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 0913 397 864 / 0911 552 182 / 0972 266 675

ያኢጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁ.3 የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ክተማ ወረዳ 9 ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ያኢጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-14
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-15 09:00
  • Bid opening (note): ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ት/ጽ/ቤት የያኢ ጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር በአንድ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 03, 2026)
  • Posted at: 2026-09-03T08:31:12.000Z
← Back to all tenders