Stationery
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesOffice Machines and Accessories
Addis Ababa
More tags
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsCatering and Cafeteria ServicesFreight TransportWarehousing, Transit and Transport ServiceTransportation ServiceLabour Outsourcing ServicesCleaning and Janitorial Equipment and ServicePrinting and PublishingVehicleRentTour and TravelHospitality, Tour and TravelEvent Organizing and PlanningAdvertising and PromotionAudio Visual, Photography and Filming Service and EquipmentArtMusical InstrumentsOthersAmharic2merkatoAddis Ketema Sub City Woreda 01 Finance Bureau
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በስሩ ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የፅህፈት መሣሪያዎች /ሲፒኦ ማስያዣ ለቀረቡት ዕቃዎች ዋጋ 2%/
- ሎት 2 የጽዳት እቃዎች /ሲፒኦ ማስያዣ ለቀረቡት ዕቃዎች ዋጋ /2%/
- ሎት 3 የደንብ ልብስ /ሲፒኦ ማስያዣ ለቀረቡት ዕቃዎች ዋጋ /2%/
- ሎት 4 የህትመት ስራዎች 10,000/አስር ሺህ ብር/
- ሎት 5 የመስተንግዶ አገልግሎት 10,000 /አስር ሺህ ብር/
- ሎት 6 የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት 10,000 /አስር ሺህ ብር/
- ሎት 7 የጉልበት ስራ አገልግሎት 10,000 /አስር ሺህ ብር/
- ሎት 8 የሞንታርቦ ኪራይ እና የአዳራሽ ዲኮር አገልግሎት ለእያንዳንዱ አገልግሎት 10,000 / አስር ሺህ ብር/
አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ሲፒኦ ማሰራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
- የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የገበሩ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- በመንግስት ግዥ የአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ወረቀት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ለተቀመጡት ዝርዝሮች ያስገቡትን የዕቃ ዋጋ 2% እና ሌሎች ለተዘረዘሩ አገልግሎቶች በየሎቱ በተገለጸው የብር መጠን መሰረት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ሲፒኦ ማሰራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ለሚሰሩ ከስራና ክህሎት ጽ/ቤት የትብብር ደብዳቤ በማምጣት በተፈቀደላቸው ዘርፍ ላይ ብቻ ያለ ክፍያ የጨረታ ሰነድ መውሰድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሳያሲዙ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ከሚያመርቱት ምርት ውጭ በሆነ ዕቃዎች ላይ እንደማንኛውም ነጋዴ የጨረታ ሰነድ መግዛትና ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ፣ስርዝ ድልዝ የሌለው ዋጋ መሙላትና ሙሉ የጨረታ ሰነዱን ከሚያስገቡት ዶክመንት ጋር በማያያዝ ተመላሽ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ናሙና በሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ጨረታው አየር ላይ እስከሚቆይበት ጊዜ ብቻ ናሙናውን ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ የሚቆይ ሲሆን በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ማሳሰቢያ፡- ለናሙና ማስቀመጫ በቂ ቦታ ስለሌለን የጨረታው ሂደት እንደተጠናቀቀ በ1 ወር ውስጥ ያቀረባችሁትን ናሙና እንድትረከቡ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው የንብረት ብክነት እና ብልሽት ሃላፊነት የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አድራሻ፡-ሕ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት ልዩ ቦታ
ተክለሃይማኖት በርበሬ በረንዳ
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-15
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ የሚቆይ ሲሆን በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-15 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ የሚቆይ ሲሆን በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ketema Sub City Woreda 01 Finance Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 03, 2026)
- Posted at: 2026-09-03T09:48:30.000Z