Stationery
በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ የተለያዩ የሕክምና አላቂና ቋሚ እቃ፣ የፅሕፈት መሣሪያዎች፣ ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና ስፌት፣ የኅትመት ሥራዎች፣ ፈርኒቸር፣ የትራንስፖርት እና ጥገና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የ1ኛ ዙር ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 1/19
በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አገልግሎት ላይ የሚውሉ
- የተለያዩ የሕክምና አላቂና ቋሚ እቃ የፅሕፈት መሣሪያዎች፤
- ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- የፅዳት እቃዎች፣
- የደንብ ልብስ እና ስፌት፣
- የህትመት ሥራዎች፤
- ፈርኒቸር፣
- የትራንስፖርት እና ጥገና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በአቅራቢዎች ዝርዘር የተመዘገቡና ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ሕጋዊ ዕውቅና ካለው ባንክ ሲፒኦ በማቅረብ በ15 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈፀም የሚችል መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ፣ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ብሎ በመለየት ለየብቻው በጥንቃቄ በ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በየሎቱ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ጨረታው ከወጣበትቀን ጀምሮ ባሉት /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን የአንዱን ዋጋ ቫትን ያካተተ በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 10 የሥራ ቀናት የተዘጋጀውን ሰነድ ከየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ላይ የረዳት ፋይናንስ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 413 ቀርበው በየሎቱ 100.00 /አንድ መቶ/ ብር ከፍለው ሰነዱን በመውሰድ
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል የሚጫረቱበት እንደየሎቱ በተዘረዘረው መሠረት
- 5000/ አምስት ሺህ ብር ብቻ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት 1
- 8000/ስምንት ሺህ ብር ብቻ/ ፣ ለፅዳት እቃዎች ሎት 2
- 5000/አምስት ሺህ ብር ብቻ/ የደንብ ልብስ ሎት 3
- 10,000.00/ አስር ሺህ ብር/ ቋሚ እቃ፣ ፈርኒቸር፣ ሎት 4
- 10,000.00 /አስር ሺህ ብር ብቻ/ ፣ የኤሌክትሮኒስ ሎት 5
- 5000/አምስት ሺህ ብር ብቻ/ ለህትመት ሥራዎች ሎት 6
- 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ የሕክምና አላቂና ቋሚ እቃ ሎት 7
- 5000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ የደንብ ልብስ ስፌት ሎት 8
- 5000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ/፤ የትራንስፖርት ጥገና አገልግሎት ሎት 9
በጨፌ ጤና ጣቢያ ስም ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ /CPO/ ብቻ በታሸገ ኢንሽሎፕ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ከህትመት እና ሕክምና እቃዎች ውጭ ሌሎች እቃዎች ላይ ናሙና ሳምፕል ማኑዋል ወይም ፎቶ ማቅረብ አለባቸው።
11. ተጫራቾች ከገዙበት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልተው የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
12. ጨረታውም ማስታወቂያው ከወጣበት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰአት ላይ ጨረታው ታሽጎ በዚሁ እለት 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት እለት ሕዝባዊ ሃይማኖታዊ በዓል ከሆነ ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ሌላ ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይከፈታል።
13. ተጫራቾች በጨረታው አከፋፈት ሥርዓት ላይ በራሳቸው ፍቃድ ባይገኙ ጨረታው አይስተጓጎልም።
14. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከመገናኛ ወደ ሲግናል በሚወስደው መንገድ ሱመያ መስጊድ ጀርባ ከማጂክ ት/ቤት አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡- 0116663281 ወይም የካ/ክ/ከተማ ወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ የግዥ ቡድን መሪ
በየካክ/ከተማ የወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-16
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰአት
- Bid opening: 2026-09-16 10:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡30 ሰአት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Cheffe Health Post
- Buyer address: ከመገናኛ ወደ ሲግናል በሚወስደው መንገድ ሱመያ መስጊድ ጀርባ ከማጂክ ት/ቤት አጠገብ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
- Posted at: 2026-09-04T07:49:17.000Z