Equipment and Accessories
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የቡሌ ሆራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም በከተማው ስር ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተለያዩ እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማሰታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የቡሌ ሆራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም በከተማው ስር ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቋሚ የቢሮ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር) ፣የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳትና፣ ቋሚ አላቂ እቃዎችን እንዳሁም የደንብ ልብስ፣ የሞተር ሳይክሎችን፣ የመኪና መለዋወጫዎች እና የቴክኒክ እናሙያ ማሰልጠኛ የስልጠና እቃዎች አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በየንግዱ መስኩ ሕጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃዳቸውን፣ አመታዊ የሁለት የ2019 ዓ.ም የሥራ ግብር የከፈሉበትን (ያሳደሱ)፣ በእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን እንዲውም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን የሚገልጽ መረጃ ሠነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
2. With Holding መከፈል የሚችል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በቡሌ ሆራ ገቢዎች ባለስልጣን በመክፈል በቡሌ ሆራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ክፍል በማቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. ማንኛውም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለቋሚ ዕቃዎችና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛዎች ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) እንዲሁም ለጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እና ቋሚ አላቂ እቃዎችና የደንብ ልብስ 10,000 (አሥር ሺህ ብር) በቡሌ ሆራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በባንኩ የተመሰከረለት (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በግልጽ በመፃፍ በአንድ (1) አንድ ኮፒና (1) ኦርጂናል በመለየት ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
6. በጥቃቅንና አስተኛ የተደራጁ ማህበራት ከሆኑ በመንግስት የግዢ መመሪያ መሰረት ይበረታታል፣
7. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚህ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በቡሌ ሆራ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ይከፈታል።
8. የጨታ አሸናፊ ማሸነፉ በጽሁፍ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በዐ ቀን ውስጥ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ በባንክ በተመረተ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ በማስያዥከመስሪያ ቤቱ ጋር መፈራረም አለበት።
9. አሸናፊው እንዲታወቅ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል።
10. ያሸነፉትን እቃዎች በሱራ ትራንስፖርት እስከ መስሪያ ቤቱ ግምጃ ቤት ማምጣት እና ፈርኒቸር እቃዎችን በራሱ ወጪ መገጣጠም የሚችል።
11. ተጫራቾቹ በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስረዓት ላይ ካልተገኙ ፖስታው አይከፈትም።
12. የመልካም ስራ አፈፃፀም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ ቁጥር፡- 046-443-06-12 /09 –19-98-65-61/09-16-83-58-39
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የቡሌ ሆራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-22 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Bule Hora Woreda F/E/D/Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
- Posted at: 2026-09-04T07:57:43.000Z