Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በምዕራብ አርሲ ዞን ቆሬ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና ጽህፈት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ ህጋዊና አቅም ያላቸውን ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕራብ አርሲ ዞን ቆሬ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች 1ኛ ዙር በ2019 የበጀት ዓመት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማለትም

  • ኤሌክትሮኒክስ
  • ፈርኒቸር
  • የፅዳት ዕቃዎች
  • የደንብ ልብስ
  • የጽህፈት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ ህጋዊና አቅም ያላቸውን ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ /መስፈርት / በመከተል ይህን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን (2018 /2019) ግብር የከፈሉ አንዲሁም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ቫት ከፋይ የሆኑ/ TIN Number/ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ማንኛውም ተጫራች ወደ ጨረታው ሂደት ከገባ በኋላ በሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች ማሻሻል መቀየር እንዲሁም ሀሳቤን ቀይሬአለሁ ማለት አይችልም።

3. ማንኛውም ዕጩ ተወዳዳሪ የጨረታውን ሂደት ለማስተጓጎል ቢሞክር ከጨረታው ውጪ እንዲሆን ተደረጎ ወደፊትም በሚደረገው የመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ የሚደረግ እና ያስዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ የሚሆን ይሆናል።

4. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ እንዲችል የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።

5. ተጫራቾች በሚሰሩበት የንግድ እና በንግድ ፍቃዳቻው ዘርፍ ብቻ ነው መወዳደር የሚችሉት።

6. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለያንዳንዱ የግዥ መደብ ብር 10000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተመሰከረለት CPO ማቅረብ አለበት ነገር ግን በካሽ ከሆነ ቆሬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000080903468 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆሬ ቅርንጫፍ ገቢ ተደርጎ computer generated slip መቅረብ አለበት።

7. ተወዳዳሪ ድርጅቶች የዕቃ ጥራት ደረጃቸው አስቸጋሪ የሆነ የዕቃ አይነቶችን መስሪያቤታችን ቀድሞ ስላዘጋጀ ለምሣሌ የኮሚፕውተር ወረቀት ፣እስክሪብቶዎች፣ ኡሁ ፣ አጀንዳ፣ የኮምፒውተር ቀለም ኦርጅናል፣ የቆዳ ውጤቶች ቦርሳዎች እና ሌሎችም ተወዳዳሪ ድርጅቶች ይህን ናሙና መሰረት በማድረግ ብቻ የምንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።

8. አሸናፊው ድርጅት ዕቃውን ጭነው እስከ መ/ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት።

9. ተጫራቾች ዕቃው የተሰራበትን /የተመረተበትን ሀገርና የጥራት ደረጃ የመስራት አቅሙን እንዲሁም ሞዴሉንና የተመረተበት ዓ.ም መግለፅ አለባቸው።

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጂናል በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።

11. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን መሙላት ያለባቸው በተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት እንዲሁም እያንዳንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት። በራሳቸው ሰነድ ላይ የሚሞላ ለስራችንአመቺ ስለማይሆን ተቀባይነት የለውም።

12, ጽ/ቤታችን የሚያጫርታቸውን እቃዎች እስከ 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።

13. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ሙሉ አድራሻቸውን ፣ስልክ ቁጥራቸውን በትክክል ጽፈው መፈረምና ማህተም ማድረግ አለባቸው።

14. ተወዳዳሪዎች የሚሰጡት የጨረታ ዋጋው ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት።

15. መ/ቤቱ ጨረታውን ገምግሞ ለማሳለፍ ወይም ውድቅ ለማድረግ የሚጠቀምበት ዘዴ እንደ እቃው አይነት ወይም የሚፈለገው አገልግሎትን መሰረት በማድረግ ጥራትን ወይም ዋጋን ከግንዛቤ በማስገባት ተወዳዳሪዎችን አሸናፊ ወይም ውድቅ የሚያደርግ ሲሆን ሁለት እኩል ዋጋ ቢያቀረቡ በብዛት ላሸነፈው የሚሰጥ ይሆናል።

16, ሰነዱ ሽያጭ የሚቆይበት ቀን 29/12/2018 እስከ 18/1/2019 ሲሆን በ4፡00 ላይ ሳጥኑ ተዘግቶ ጨረታውን የሚከፈተው በ18/1/2019 ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኘበት በቆሬ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በይፋ ይከፈታል። በዕለቱ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።

17. የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ከቆሬ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በቆሬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በባንክ መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000080903468 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ስሊፕ በመያዝ ቢሮ ቁጥር 04 ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ተወዳዳሪ ድርጅቶች ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ በተዘጋጀለት የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰአት የሰነዱ ሽያጭ እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ማስገባት ይችላል።

18. የጨረታ ውል ከጨረታ ሰነድ ጋር ስለሚሸጥ በውሉ መሰረት ጨረታውን ያሸነፈው ነጋዴ ለውሉ ተገዥ መሆን አለበት።

19. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

20. አሸናፊ ድርጅቶች ካሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ ቆሬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000080903468 በኢትዮጵያ ንግድ ገቢ ማድረግ አለበት።

ለበለጠ መረጃ ሞባይል 0924300123/0966253235

የምዕራብ አርሲ ቆሬ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-28 10:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: West Arsi Zone Kore Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
  • Posted at: 2026-09-04T08:22:43.000Z
← Back to all tenders