Building Construction
በኢሉ አባቦር ዞን ዶረኒ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የመሶብ አገልግሎት ማዕከል ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢሉ አባቦር ዞን ዶረኒ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በዶረኒ ወረዳ ኤሌሞ ከተማ ባለ 3 ደረጃ በ 730 ቀናት ተገንብተው የሚጠናቀቅ የመሶብ አገልግሎት ማዕከል ግንባታ የሚከተሉትን መስፈርቱን ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰገንባት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ደርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፤
1. ተጫራቾች ከኦሮሚያ ኮንትራክሽን ባለስልጣን ወይም ከፌዴራል ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ2019 የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ በ GC‐4/BC-3 ዘርፍ እና ከዛ በላይ ማቅረብ የሚችል፤
II ከገቢዎች ባለስልጣን የተሰጠ የቫት እና የግብር ከፋይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
III. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፤ ግብር የከፈለና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
IV.የ2018 ከታክስ ነፃ ሰርተፍኬት ከሀገር ውስጥ ገቢዎች ባለስልጣን ማቅረብ የሚችል
V. በኢትዮጵያ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዘገቡ መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
2. ጨረታው በብሔራዊ ጨረታ መወዳደሪያ መሰረት የሚካሄድ ሲሆን ፣ለሀገር ውስጥ ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ለይ በተገለፀው መሰረት ይሆናል፡፡
3. ለጨረታ ማስከበሪያ የ500,000(አምስት መቶ ሺህ) ብር CPO በዶረኒ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ባንክ አሰርተው ማቅረብ የሚችል፤
4. ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ከጥላላ ሂሳብ 10 በመቶ (Performance Bond) በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ዉል የሚፈራረም ይሆናል፡፡
5. መስፈርቱን ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታውን ተጨማሪ መረጃና የጨረታ ሰነድ ከዶረኒ ወረዳ ግዥ ክፍል በመንግስት የስራ ሰዓት በመቅረብ 3500(ሶስት ሺህ አምስት መቶ) ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000289247697 ላይ በማስገባት የገቢ ደረሰኝ ከወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን በማቅርብ መግዛት ይችላሉ፤
6. በዚህ ጨረታ የመሳተፍ ድርጅት በዶረኒ ወረዳ አስተዳደር በመገኘት የቦታ ጉብኝት (Site Visit) በማድረግ የጉብኝት የምስክር ወረቀት ከመስሪያ ቤታችን በመውሰድ የቴክኒክ ሰነድ ውስጥ አሽገው ማቅረብ አለበት፤
7. የቴክኒክና ፋይናንስ ዶከመንቶች እንዴት እንደሚቀርብ፡
A የዋናውና ኮፒ የቴክኒክ ብቃት ሰነዶች ተለይተው በተዘጋው ኤንቨሎፕ ውስጥ “ዋናና ኮፒ የቴክኒክ ብቃት ሰነዶች“ ተብለው በተፈረመበት ኤንቨሎፕ ውስጥ ሁለቱም ከታሸገ በኋላ በትልቅ ኤንቨሎፕ ውስጥ መታሸግ አለበት፤ ይህ የውጪው ኤንቨሎፕ የአቅራቢ አድራሻና ሌሎች መረጃዎች በጨረታው ላይ የተመለከቱ የምስክር ወረቀት የሚይዝ ሲሆን ፤ በጨረታ ኮሚቴ ብቻ የሚከፈት ተብለው በግልጽ የሚጻፍ ሲሆን ፤የጨረታ ማሰከበሪያ (CPO ) ሰነድ ለብቻ ታሽገው ከዋናው የቴክኒክ ሰነድ ጋር ይቀመጣል፡፡
B. የዋናውና ኮፒ የፋይናንስ አቅርቦት ተለይተው በተዘጋው ኤንቨሎፕ ውስጥ “ዋናና ኮፒ የፋይናንስ አቅርቦት ተብለው በተፈረመበት ኤንቨሎፕ ውስጥ ሁለቱም ከታሸገ በኋላ በትልቅ ኤንቨሎፕ ውስጥ መታሸግ አለበት፤ ይህ የውጪው ኤንቨሎፕ የአቀራቢ አድራሻና ሌሎች መረጃዎች በጨረታው ላይ የተመለከቱ የምስክር ወረቀት የሚይዝ ሲሆን ፤ በጨረታ ኮሚቴ ብቻ የሚከፈት ተብለው በግልጽ መጻፍ አለበት፡፡
C. ሁለቱም የቴክኒክ እና ፋይናንስ ፕሮፖዛል ውስጥ በትልቅ ኤንቨሎፕ ውስጥ የሚቀመጥ ሲሆን ፣ ይህ የውጪው ኤንቨሎፕ የአቅራቢ አድራሻና ሌሎች የምስክር ወረቀት ለይ በተመለከቱ መረጃዎችን የሚይዝ አና በጨረታ ኮሚቴ ብቻ የሚከፈት ተብለው መጻፍ አለበት፡፡
D. ማህተምና ፊርማ በተወዳዳሪዎች መመሪያ ላይ በተገለጸው መሰረት መሆን አለበት፤
E. የጨረታ ሰነድ አዘገጃጀት ላይ ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ ያለውን የጨረታ ሰነድ ማጥናት ይጠበቅባቸዋል፡፡
F. የፋይናንስ አቅርቦት ሰነድ ኦዲተር ወይም ለዚህ ጉዳይ ኃላፊነት በተሰጠው ኮሚቴ ባለበት የቴክኒከ ብቃት ሰነዶች እስከሚታይ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ተዘግተው ይቆያል፡፡
G. ሀላፊነት ባለው አካል የተመደበ ኮሚቴ የጨረታ ሰነዱን መሰረት በማድረግ የተጫራቾችን ብቃት ይመዝናል፤ ከቀረቡት ተጫራቾች የግዴታ መስፈርቶችና የቴክኒክ መስፈርቶችን ያሟሉ ተወዳዳሪዎች ብቻ ተለይተው ስም ዝርዝራቸው በይፋ እንዲለጠፍ የደረጋል፡፡
H. ሀላፊነት ባለው አካል የተመደበ ኮሚቴ የፋይናንስ አቅርቦት ሰነድ ከመከፈቱ በፊት የቴክኒክና የግዴታ መስፈርቱን ላሟሉ ተጫራቾች ብቻ የፋይናንስ አቅርቦት ሰነዱ የሚከፈበትን ቀንና ሰዓት ያሳውቃል፡፡
I. የሀሰት ሰነድ ወይም የቴክኒክ ሰነድ ላይ የፋይናንስ አቅርቦት ለማሳየት ከተሞከረ ጨረታውን እንዲሰረዝ ያደርጋል፡፡
J. ተወዳዳሪው በቴክኒክ ብቃት ሰነድ ዉስጥ የፋይናንስ አቅርቦት ሰነድ ኤንቨሎፕ ወይም በተቃራኒው ተደርገው ስህተት ከተፈጠረ ኮሚቴው ሃላፊነቱን አይቀበልም፡፡
8. ጨረታው ይህ ማስታውቂያው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውለው በ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግተው ከጠዋቱ 4፡30 ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ 22ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የመንግስት ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግተው እንዲከፈት ይደረጋል፡፡ ሁሉም ጨረታ ከተገለጸው የጨረታ ማስከበሪያ ጋር መሆን አለበት፡፡ ጊዜውን አሳልፈው የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት የለውም፡፡ ይህ ጨረታ ተወዳዳሪዎች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዶረኒ ወረዳ ምክትል አስተዳደርና ግብርና ጽ/ቤት የሚከፈት ይሆናል፤
9. ጨረታው ስራ ላይ መዋል ያለበት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 120 ቀናት መሃል ይሆናል፡፡
10. ጽ/ቤቱ የተገኘውን አማራጭ ካገኘ ይህንን ጨረታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት ይኖራል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር
የዶረኒ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር 0917276787/0913308131
የዶረኒ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር 0912914789
በኢሉ አባቦር ዞን አስተዳደር የዶረኒ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-25
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውለው በ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-09-25 12:00
- Bid opening (note): በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውለው በ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Doreni District Finance and Economic Development Office
- Bid bond: 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 3500 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ) ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
- Posted at: 2026-09-04T08:25:55.000Z