Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የማነብርሃን ቅድመ አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፦ 001/2019

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የማነብርሃን ቅድመ አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ 10,000
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች 8,000
  • ሎት 3 የህትመት 3,000
  • ሎት 4 የቀይ መስቀል ዕቃዎች 2000
  • ሎት 5 የትምህርት አላቂ ዕቃዎች 7,000
  • ሎት 6 የፅዳት ዕቃዎች 6,000
  • ሎት 7 የፕላንትና ማሽነሪ ዕቃዎች 20,000
  • ሎት 8 ቋሚ ዕቃዎች 15,000
  • ሎት 9 ልዩ ልዩ ዕቃዎች 3,000
  • ሎት 10 የፕላንትና ማሽነሪ ጥገና 3,000
  • ሎት 11 የቁሳቁስ ጥገና 3,000
  • ሎት 12 ሚንስትሪንግ ቆሎና ውሃ 3,000
  • ሎት 13 ለመሠረ ልማት ዕድሳት እና ጥገና -7,000.00

1- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።

2. በመንግስት ግዥ ኤጄንሲ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ ኮፒ ማቅረብ የሚችል።

3.-የተጨማሪ እሴት ታክስ ፤ ቫት ተመዝጋቢ/ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) የስራ ቀናት የማይመለስ በየሎቱ 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ከግዥ ክፍል መግዛት ይችላል።

5-ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ መሙላት አለባቸው።

6-ተጫራቾች ከላይ በየሎቱ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።

7-ናሙና ለሚያስፈልጋቸው የዕቃ አይነቶች ተጫራቾች ጨረታው ከመዘጋቱ ቀደም ብለው የናሙናውን አይነት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙና ለማቅርብባቸው(በፎቶ) የእቃ አይነቶች በሚቀርበው የእቃ መግለጫ (specification) መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙናዎች በጨረታ ውል ተሸናፊ ተጫራቾች ተመላሽ ይሆናል።

8. የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ቫት/ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እንዲሁም ለጥቃቅን እና አንስተኛ ከአደራጃቸው አካል ደብዳቤ እና ደብዳቤው ሼድ እንዳላቸው የሚገልፅ መሆኑን አያይዘው ማቅረብ የሚችል፣ ሲሆን በተጨማሪ በሚያመርቱት፣ ዕቃ ብቻ በደብዳቤ ዋስትና የተሰጠበት ገንዘብ መጠን መጥቀስ ማህበራቱን በአደራጃቸው መስሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ የተፈረመበት መሆን አለበት።

9. አሸናፊው ያሸነፈበትን እቃ ትምህርት ቤቱ የእቃ መረከቢያ እስቶር ድረስ በራሱ ትራንስፖርት በማቅረብ ማስረከብ ይኖርበታል።

10. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት በአስራ አንደኛው (11) ቀን በአራት ሰዓት (4) ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን (4፡30) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

11. አሸናፊው ውል ገብቶ እቃዎቹን ከማስገባቱ በፊት የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለበት።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊልየመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር፡- 09 01 40 40 07/ 011 349 0678

አድራሻ፡- ወይራ ሰፈር አደባባይ ኮንደምኒየም ፊት ለፊት

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የማነብርሃን ቅድመ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው (11) ቀን በአራት ሰዓት (4:00)
  • Bid opening: 2026-09-16 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው (11) ቀን በአራት ሰዓት (4:30)
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yemane Berhan Kindergarten and Primary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
  • Posted at: 2026-09-04T08:35:46.000Z
← Back to all tenders