Stationery

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የአቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተለያዩ ለቢሮ መገልገያ የሚውሉ ዕቃዎች ግዥ እንዲሁም የተለያዩ ማሽኖች ዶዘር፣ እስካቫተር፣ ግሬደር፣ ፒካፕ እና ሲኖትራክ ለመከራየት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የአቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተለያዩ ለቢሮ መገልገያ የሚውሉ

  • የጽሕፈት መሣሪያዎች፣
  • አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፤
  • የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፤
  • የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤
  • የተሽከርካሪ ጎማዎች፤
  • የሞተር ሳይክል ጎማዎች፤
  • የቢሮ ፈርኒቸሮች በግልጽ ጨረታ ሕጋዊንግድ ፍቃድ ያላቸውን አቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
  • እንዲሁም የተለያዩ ማሸኖች ዶዘር፤
  • እስካቫተር ፤
  • ግሬደር፤ ፒካፕ እና
  • ሲኖትራክ ለመከራየት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር የምትችሉ መሆናችሁን እንገልጻለን።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. የ2018 የመንግሥት ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ከፌዴራል ወይም ከክልል ገንዘብ ቢሮ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የተ.እ.ታ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና 3 % ለመንግሥት ለመቁረጥ ፍቃደኛ የሆኑና የንግድ መለያ ቁጥር (TN Number ) ያላቸው ሆኖ ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  5. ማንኛውም ተጫራች መሥሪያ ቤቱ በሚያወጣው መመሪያና መስፈርት ግዴታ መወጣት አለበት።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ፦
    • ለጽሕፈት መሣሪያዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች - ብር 17,000.00 (አስራ ሰባት ሺህ)
    • ለሠራተኞች የደንብ ልብስ - ብር 5,000.00 ( አምስት ሺህ)
    • ለኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች - ብር 20,000.00 ( ሃያ ሺህ)
    • ለቢሮ ፈርኒቸሮች - ብር 8,000.00 ( ስምንት ሺህ)
    • ለግንባታ ለሚውሉ መሣሪያዎች - ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ)
    • የተለያዩ የመኪናና የሞተር ሳይክል ጎማዎች - ብር 14,000.00( አስራ አራት ሺህ)
    • ለተለያዩ ማሽኖች 50,000.00 ሃምሳ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
  7. የጨረታው ሰነድ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በአቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀን (በአስራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ቀን ከ2፡30 -11፡30 ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫት (VAT/ 15%) ያካተተ መሆን አለበት።
  9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም አሽገው ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  10. ያስቀመጥነው የዕቃ ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ መጨመር እና መቀነስም ይቻላል።
  11. ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉበትን የቢሮ ፈርኒቸሮችን (Furniture) ገጥመው ማስረከብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  12. ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን 16 ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግተው በዕለቱ 4፡30 በአቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ጨረታው ላይ ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግድም።
  13. ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎች እስከ አቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ ቤት ድርስ በራሳቸው ወጪና ትራንስፖርት ያቀርባሉ።
  14. ተጫራቾች ዕቃዎቹን የሚያስረክቡበት በቱሉ ዋዩ ከተማ አቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ ቤት ንብረት ክፍል ሆኖ አሸናፊዎቹ በተዋዋሉበት ውል መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  15. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡-ስልክ ቁጥር 0910266687/0913407800 ደውለው መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በሆሮ ጉዱሩ መለጋ ዞን የአቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-22
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-22 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Horo Guduru Wollega Zone Abe Dengoro Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
  • Posted at: 2026-09-04T08:56:07.000Z
← Back to all tenders