Materials

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር የሚገኘው የአብዮት ፋና ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር የሚገኘው የአብዮት ፋና ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ የትምህርት መሳሪያ እቃዎች ፣አላቂ የቢሮ እቃዎች የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፈርኒቸሮች፣የደንብ ልብስ፣የስፖርት እቃዎችን እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገናዎች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. በመንግስት የግዢ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው።

3. በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4. የጨረታ ሰነዶቻቸውን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ በት/ቤቱ ሒሳብ ክፍል ውስጥ ለዚህ በተዘጋጅ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል ዋጋ ሎት1. ለደንብ ልብስ 22,831.82.(ሃያ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ አንድ ብርከ82/100)፣ ሎት02 የተለያዩ የትምህርት መሳሪያ እቃዎች እና አላቂ የቢሮ እቃዎች 36,091.61(ሰላሳ ስድስት ሺህ ዘጠና አንድ ብር ከ61/100)፣ ሎት03 የህክምና እቃዎች 345.12 (ሶስት መቶ አርባ አምስት ብር ከ12/100)፤ ሎት04 የፅዳት እቃዎች 21,280.84 (ሃያ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰማኒያ ብር ከ84/100) እና ሎት ሎት 05 ህትመት 1,446.42 (አንድ ሽህ አራት መቶ አርባ ስድስት ብር ከ42/100) ሎት 06 ቋሚ እቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 8,520.00 (ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሀያ ብር) ሎት 07. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገናዎች 2,520.00 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሃያ ብር) ብቻ አብዮት ፋና ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በሚል ሲፒኦ በማሰራት ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከአብዮት ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

6. ጥቃቅንና አነስተኛ ካደራጃቸው ተቋም ለጨረታ ማስከበሪያ ደብዳቤ ለአብዮት ፋና የሚል ዋናውን ማቅረብ አለባቸው።

7. ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጭ ሞልቶ ያመጣ ተቀባይነት የለውም።

8. ተጫራቾች የእቃውን ሳምፕል (ናሙና) ማስገባት አለባቸው።

9. ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ማስገባት ሲቻል በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ይታሸጋል።

10. ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር-1 ውስጥ ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ከብሔረ ፅጌ መናፈሻ አካባቢ በግራ በኩል አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ቆዳ ፋብሪካ ቀጥሎ።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለጎት፡-

ስልክ ቁጥር: 0114 425 667 / 0114 431 761 / 0114 666 735

አብዮት ፋና ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-15
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ማስገባት ሲቻል በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-16 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Abiyot Fana Elementary School
  • Buyer address: ከብሔረ ፅጌ መናፈሻ አካባቢ በግራ በኩል አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ቆዳ ፍብሪካ ቀጥሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
  • Posted at: 2026-09-04T09:11:05.000Z
← Back to all tenders