Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የቦሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የቦሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በቁጥር 001/2019ዓ.ም የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1 ሎት 1 የደንብ ልብስ 7000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ

2/ ሎት 2 አላቂ ጽህፈት መሳሪያዎች 8000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ

3/ ሎት 3 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች 7000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ

4/ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ 5000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ

5/ ሎት 5 የህንጻ ቁሳቁስና ተገጣጣሚ እቃዎች 6004.05 ብር የጨረታ ማስከበሪያ

6/ ሎት 6 ህትመት 4000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1. በሚጫረቱበት ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር እቃ አቅራቢዎች የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ ሆነው ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋም ካደራጃቸው አካል የአምራችነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች በምድብ 1፤ 2፤ 3፣4፤ 5፣6 የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በተቋቋሙበት የንግድ ዘርፍ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች በዝርዝሩ መሰረት ዋጋ ሞልተው የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናልና ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሰነዱ ታሽጎ ባይቀርብ እና ተፈላጊ ሰነዶች ቢጎድሉ ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል።

4. የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በየሎቱ ላይ በተገለፀው መሰረት እያንዳንዱ የሎት ዋጋ ብር በባንክ በተመሰከረ /ሲፒኦ/ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ብዛቱ ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ የሚችለው 20% ነው።

6. አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስገባት አለባቸው።

7. የጨረታ ሰነዱ ስርዝድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናል።

ማንኛውም ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 10፡00 ሰዓት ማስገባት የሚችል ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻና መዝጊያ በስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥሉት የስራ ቀን ይሆናል፡፡ ለእያንዳንዱ ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ቁሳቁሶች ሳምፕል /ናሙና/ ከነማብራሪያው ከጨረታ ዶክመንት ጋር አብሮ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡ ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መ/ቤቱ ባቀረበው እስፔሲፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116 393 119

አድራሻ፡- ከቦሌ ከመድሐኒአለም ቤተክርስትያን ወደ 22 ማዞሪያ በሚወስደው መንገድ አለምነሽ ፕላዛ ህንፃ ፊት ለፊት

የቦሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-15
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 10፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-16 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bole Higher Secondary School
  • Buyer address: ከቦሌ ከመድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ወደ 22 ማዞሪያ በሚወስደው መንገድ አለምነሸ ፕላዛ ህንፃ ፊት ለፊት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዳቸው
  • Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
  • Posted at: 2026-09-04T09:13:47.000Z
← Back to all tenders