Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የሽመልስ ሀብቴ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም. የተለያዩ ዕቃዎች በመስኩ የተሰማሩ ነጋዴዎች ባለሙያዎችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛትና ማሠራት ይፈልጋል
Cleaning and Janitorial Equipment and ServiceStationeryOffice Supplies and Services
Addis Ababa
More tags
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsSport Materials and EquipmentBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksPlastic ProductsPlastic Raw Materials and ProductsPlastic Raw MaterialsPrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and PublishingEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsConstruction Machinery and EquipmentHouse FurnitureFurniture and FurnishingOffice FurnitureComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOthersMaintenance and RepairHand Tools and Workshop EquipmentCarpets and CurtainsFoam MattressMaterialsEducation and TrainingAmharic2merkatoShemelese Habte Elementary School
Description
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
የሽመልስ ሀብቴ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የጽሕፈት ዕቃዎችን፣ የፅዳት ዕቃዎችን፣ የደንብ ልብስ፣ የስፖርት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሕንፃ መሣሪያዎች፣ የሕፃናት ዴኬር ዕቃዎች፣ የሕትመት ሥራዎች፣ የጥገና ሥራዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች በመስኩ የተሰማሩ ነጋዴዎች ባለሙያዎችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛትና ማሠራት ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
የሎት ዓይነት |
ማስያዣ (CPO) |
|
1 |
ለሎት 1. የጽሕፈት ዕቃዎች ፣ ለሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች |
1000.00 |
|
2 |
ለሎት 3 የደንብ ልብስ ዕቃዎች |
1500.00 |
|
3 |
ለሎት 4 የስፖርት ዕቃዎች፣ ለሎት 5 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ለሎት 6 የሕንፃ መሣሪያዎች፣ ለሎት 7 የሕፃናት ዴኬር ዕቃዎች |
1500.00
|
|
4 |
ለሎት 8 ቋሚ እቃዎች |
1000.00 |
|
5 |
ሎት 9 የጥገና ሥራዎች |
1500.000 |
|
6 |
ሎት 10 የሕትመት ሥራዎች |
1000.00 |
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
- ተጫራቾች ለጨረታ ሲመጡ የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የተሰማሩበት የሥራ መስክ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና በምታስገቡት ሰነድ ላይ በእያንዳንዱ ፔጅ ላይ የድርጅቱን ክብ ማህተም ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡ ከሌላችሁ ብትወዳደሩም መሥሪያ ቤቱ ውድቅ የሚያደርግ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
- በተጠቀሰው እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የጨረታ ሰርተፍኬት ያለው።
- ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰነድ የሚያስገቡበት ወቅት ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ካላቀረበ ውድቅ የምናደርግ መሆኑን እንገልጻለን።
- ዕቃዎቹን በመ/ቤቱ የግዥ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፍል መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ማወዳደሪያ የአንዱ ዋጋ /ቫት/ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለበት።
- ቫትን ያላካተተ ከሆነ ቫት እንዳካተተ ይቆጠርበታል።
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተረጋገጠበት በ5 ቀን ውል መፈፀምና 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነዳቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገው ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዛው ዕለት በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በሚቀጥለው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከላንድማርክ ሆስፒታል አጠገብ ቂ/ክ/ከ/አስ ሽመልስ ሀብቴ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
ስልክ ቁጥር / 011 5 51 94 13/0115 57 44 67
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክ/ከተማ/የሽመልስ ሀብቴ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-15
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-16 10:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በሚቀጥለው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Shemelese Habte Elementary School
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 250.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
- Posted at: 2026-09-04T09:21:25.000Z