Construction Machinery
በጅማ ዞን የስግሞ ወረዳ የመንገድና ሎጅስቲክስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የግሬደር፣ ኤክስካቫተር፣ ሲኖትራክ፣ ሩሎ፣ ሻወር ትራክ እና ፒካፕ ሰርቪስ አገልግሎት አቅርቦት በሰዓት እና በቀን ለመከራየት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በጅማ ዞን የስግሞ ወረዳ የመንገድና ሎጅስቲክስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የግሬደር፣ ኤክስካቫተር፣ ሲኖትራክ፣ ሩሎ፣ ሻወር ትራክ እና ፒካፕ ሰርቪስ አገልግሎት አቅርቦት በሰዓት እና በቀን ለመከራየት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እጩዎች ማወዳደር ይችላሉ።
1. የአገልግሎት/ የማሽን አይነትን በቀጥታ የሚገልጽ አዲስ ወይም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና በQR.ኮድ የታተመ ደረሰኝ ኮፒ ማቅረብ የሚችል።
3. ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው።
4. በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ የአቅርቦት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
5. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ማቅረብ የሚችል።
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከስግሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ ብር) በመክፈል በቀን 29/12/2018 እስከ 14/1/2019 ድረስ መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ማሽኖቹን የሚገልጹ ሰነዶችን በሙሉ ማቅረብ አለባቸው ። የተከራዩ ከሆነ ከአከራይ ድርጅት የኪራይ ውል ማቅረብ አለባቸው።
8. አሸናፊው ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ቀርቦ ስምምነቱን ከስግሞ ወረዳ መንገድና ሎጅስቲክስ ጽ/ቤት ጋር ይፈርማል።
9. የጨረታው አሸናፊ ማሽነሪውን እስከ ስግሞ ወረዳ ድረስ ስራው ወደሚሰራበት ቦታ ማስረከብ አለበት። ይህ ማሽን ጽ/ቤት በሚጠይቀው ጊዜ የአየር ሁኔታ ጋር የተያያዘ መሆን አለበት።
10. በማህበሩ የተደራጁ እጩዎች የማህበሩን ህጋዊ አካል የሚገልጽ አዲስ ወይም የታደሰ ሰርተፍኬት እና በማደራጃው አካል የተሰጠ የማህበሩን የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ በፖስታ በማድረግ ሙሉ አድራሻ እና ስም በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 14/1/2019 ዓ.ም ድረስ ማስገባት አለባቸው።
12. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱን ማህተም፣ የተጫራቾች ስም እና ፊርማ መያዝ አለባቸው።
13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 14/1/2019 በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በቀን 14/1/2019 ዓ.ም በ5፡30 ሰዓት ይከፈታል።
14. ጽ/ ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ሌሎች አማራጮች ካገኘ ለበለጠ መረጃ፡ 09 65 79 11 57፣ 09 12 10 94 50፣ 09 89 03 80 40 ይደውሉ።
በጅማ ዞን የስግሞ ወረዳ የመንገድና ሎጅስቲክስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-24
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-09-24 11:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: በጅማ ዞን የስግሞ ወረዳ የመንገድና ሎጅስቲክስ ጽ/ቤት
- Bid bond: 300,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
- Posted at: 2026-09-04T09:25:03.000Z