Textile, Garments and Uniforms

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የግብዓት ግዥ በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር የግብዓት ግዥ በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መሳተፍ ይችላሉ።

የሎት ምድብ

የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ

1. የደንብ ልብስ

20000

2. የጽህፈት መሳርያ

15000

3. የጽዳት መጠበቅያ

15000

4. የጽዳት እቃዎች

2000

5. የመኪና 

15000

6. የኤሌክትሮኒክስ

10000

7. የፈርኒቸር ግዥ

10000

8. የቢሮ መስተንግዶ

3000

9. የሰራተኛ ካፍቴርያ

5000

10. የጥገና አገልግሎት ግዥ

2000

11. የትራንስፖርት ግዥ

2000

 

  1. ተጫራቾች ሕጋዊ የ2019 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
  2.  ተጫራቾች የዘመኑን የ2019 ዓ.ም ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች TIN number ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች ከአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የMA ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  5. የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ 200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 09 መዉሰድ ይችላሉ።
  6. ከሎት 1-7 ላሉት ግዥዎች ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ላሸነፉት የእቃዉን ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ከዉል ጋር ማቅረብ አለባቸዉ።
  7. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ10ኛው የሥራ ቀን በ11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣዩ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም (ሕጋዊ) ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 09 ይከፈታል።
  9. በጨረታው የተሳተፉት ሁሉም አቅራቢዎች ሰነዳቸውን ሞልተው ካስገቡ በኻላ ተጫራቾች ወኪሎቻቸዉ እንዲገኙ በማድረግ ይከፈታል።
  10. ዕለቱ በበዓላት ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይከፈታል።
  11. ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ተጫራች ድርጅቶች ለእቃ ማጓጓዣ የትራንስፖርት አገልግሎት በራሳቸዉ ወጪ መሸፈን ይጠበቅባቸዋል።
  13. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ 4 ድረስ ላሉት ሰነድ በሚያስገቡበት ወቅት ሳምፕል ማቅረብ አለባቸዉ
  14. ተጫራቾች ከአንድ እስከ አስር /1-10/ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በኦሪጅናልና በኮፒ ማቅረብ የሚችሉ

አድራሻ፡- ጎላ ፓርክ ፊት ለፊት

በስልክ ቁጥር 011-554-1638

የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ10ኛው የሥራ ቀን በ11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-17 10:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ10ኛው የሥራ ቀን በ11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣዩ ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Lessan (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T07:55:19.000Z
← Back to all tenders