Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ኢትዮ ቻይና ወዳጅነት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ዓ/ም በጀት አመት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ኢትዮቻይና ወዳጅነት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ዓ/ም በጀት አመት የ1ኛ ዙር ጥቅል ጨረታ ግዢ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። 

የሎት ዝርዝር ፡-

  • ሎት 1 አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 2 የፅዳት እቃዎች፣
  • ሎት 3 የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት 5 የፈርኒቸር እቃዎች፣
  • ሎት 6 የህከምና እቃ መገልገያዎች ናቸው።

ስለሆነም ከዚህበታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

1. ህጋዊ የሆነና የታደሰ የንግድፍቃድ ያላቸውና የዘመኑንግብር የከፈሉ በመንግስት ግ/ን/አስ ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ። እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ የምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችል።

2. ተወዳዳሪው የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት።

3. ተጫራቹ የንግድ ሰርተፍኬት ከግብርሰብሳቢ ክፍል የተሰጠውን ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ በየሎቱ 1% ተደርጎ የተሰላ ብር ለሎት 1 40000፣ ለሎት2 –43000 ለሎት 3 =48999.99 ፣ለሎት4 20000 ፣ለሎት 5 20000 ፣ለሎት 6 11307.8 ብር ህጋዊነቱ ከታወቀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ(cpo) እንደሚወዳደሩበት ሎት ብዛት አንድላይም ሆነ ለየብቻ ማሰራት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ኢትዮ ቻይና ወዳጅነት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስና ግዢ ክፍል ቢሮቁጥር 6 በመቅረብ መግዛት ትችላላችሁ።

6. ተጫራቾች ዋጋየሞሉበትን ማስረጃዎች ዋናውን እና የማይመለስ ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው።

7. ጨረታው በወጣበት በ10ኛው ቀን በ11፡00 ላይ የጨረታው ሳጥን ይታሸጋል፤ የጨረታ ሰጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውንም የተጫራቾች ማስረጃ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።

8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው ቀን ላይ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።

9. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ጠቅላላዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት ማድረግ ይኖርባቸዋል።

10. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም ሌሎች አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃዎች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ሳንፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

12. ለተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአንስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የተደራጁ ተጫራቾች ህጋዊ ማስረጃ ካደራጃቸው ተቋም የትብብር ደብዳቤ ኦሪጅናል በማምጣት ያለክፍያ ይሰጣቸዋል።

13. ለአንስተኛና ጥቃቅን ተጫራቾች 3% ልዩ አስተያየት ይደረግላቸውል። ነገርግን የእቃውን 35% ማስረጃ ማቅረብ አለበት። ወይም ከዛ በላይ ከአገር ውስጥ የታከለ እሴት መሆኑን የሚያስረዳ በተመለከተ በኦዲተር የተረጋገጠ

  • አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ሰሚት ኮንዶሚኒየም ውስጥ ሁለተኛ በር ገባ ብሎ
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116 67 76 54 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 05 ኢትዮ ቻይና ወዳጅነት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ11፡00
  • Bid opening: 2026-09-17 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ላይ ጠዋት 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethio China Friendship Primary School
  • Buyer address: ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ሰሚት ኮንዶሚኒየም ውስጥ ሁለተኛ በር ከአስፓልቱ 200 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T07:56:44.000Z
← Back to all tenders