Stationery

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 የካ ቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 የካ ቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት አመት የ1ኛ ዙር ጥቅል ጨረታ ግዢ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሎት ዝርዝር፡

  • ሎት 01 አላቂ ፅህፈት እቃዎች፣
  • ሎት 02 አላቂ የፅዳት እቃዎች፣
  • ሎት 03 የደንብ ልብስ ፣
  • ሎት 04 አላቂ የህከምና መገልገያ፣
  • ሎት 05 ኤሌክትሮኒክሶች፣
  • ሎት 06 የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ እቃዎች ፣
  • ሎት 07 የፈርኒቸር እቃዎች፣
  • ሎት 08 አላቂ የትምህርት መፅሀፎች ናቸው።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ህጋዊ የሆነና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት ግ/ን/ አስ/ኤጀንሲ ድህረገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተወዳዳሪው የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት።

3. ተጫራቹ የንግድ ሰርተፍኬት ከግብር ሰብሳቢ ክፍል የተሰጠውን ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ 1% ተደርጎ የተሰላ ብር ለሎት 1 =12,000ብር ሎት2 = 12,000 ብር፣ ሎት 3 13,000 ብር ሎት4 –4,000 ሎት5 = 45,000፣ ሎት6 =14,000፣ ሎት7 =20,000፣ ሎት8 =14,000 ህጋዊነቱ ከታወቀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ CPO/ እንደሚወዳደሩበት ሎት ብዛት አንድ ላይ ሆነ ለየብቻ ማሰራት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 / አምስት መቶ ብር / በመክፈል የካ ቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፋይናንስና ግዢ ክፍል በመቅረብ መግዛት ትችላላችሁ።

6. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ማስረጃዎች ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው።

7. ጨረታው በወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ላይ የጨረታው ሳጥን ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውንም የተጫራቾች ማስረጃ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።

8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው ቀን ላይ ጠዋት 4፡30 /ሰዓት/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።

9. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከትምህርት ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት ማድረግ ይኖርባቸዋል።

10. ትምህርትቤቱ የተሸለ ዘዴ ወይም ሌሎች አማራጮች ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በ ከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የእቃ ናሙና  ሳምፕል ማስገባት ይኖርባቸዋል።

12. ለተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድበ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የተደራጁ ተጫራቾች ህጋዊ ማስረጃ ካደራጃቸው ተቋም የትብብር ደብዳቤ ኦርጅናል በማምጣት ያለክፍያ ይሰጣቸዋል።

13. ለአነስተኛና ጥቃቅንተጫራቾች 3% ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል፡፡ ነገር ግን እቃውን 35% ወይም ከዛ በላይ ከሀገር ውስጥ እሴት ታክስ መሆኑን የሚያስረዳ በተመለከተ በኦዲተሮች የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ አለበት።

አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ልዩ ስሙ ጨሪ ።
ለበለጠ መረጃ 0116128109 ይደውሉ።
በለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 የካ ቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-17 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lemi kura Sub City Yeka Bole Secondary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T07:58:03.000Z
← Back to all tenders