Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በጉለሌ ክ/ከ/ወረዳ-1 ፋ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጉ/ክ/ከ/ወ‐1ፋ/012/2018
በጉለሌ ክ/ከ/ወረዳ-1 ፋ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል
- ሀ.አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ለ. አላቂ የፅዳት ዕቃዎች እንዲሁም
- ሒ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፤
1. በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
4. የንግድ ፍቃድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. የግዢውን መጠን እንደ አስፈላጊነቱ 20% መጨመር ወይም መቀነስ የሚቻል መሆኑን ፡፡
6. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸው ማስረጃ ከ(egp www.ppa.gov.et ) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱ በሚመለከተው ሰው ተሞልቶ ተፈርሞና ማህተም ተደርጎበት በጉ/ክ/ከ/ወ-1 ፋ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት ፡፡
8. ጨረታው የሚያበቃው በ10ኛው የሥራ ቀን 11፡00 ሰአት ሲሆን በአስራ አንደኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
9. ሁሉም ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ ናሙና ማቅረብ የሚቻል እቃዎች ላይ ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፣ ናሙና ማቅረብ ሲገባ ያልቀረበ ከሆነ ግን ተቀባይነት የለውም፤እንዲሁም ናሙና ለማቅራብ የሚያስቸግር ዕቃዎች በደንብ በሚታይ ፎቶ የተደገፈ እና በደንብ በሚተይ መልኩ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
10. አሸናፊው አቅራቢ ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት ዕቃውን ተቋሙ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም ፡፡ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. አሸናፊው አቅራቢ ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት ዕቃውን ተቋሙ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
12. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም ፡፡ ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. ጥቃቅን እና አነስተኛ በተመለከተ ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ምን አይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሃገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ/ ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፍቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ
ሀ. ሎት1 አላቂ የቢሮ ዕቃ 20000.00 / ሃያ ሺህ/ብር
ለ. ሎት2/አላቂ የፅዳት ዕቃ 22000.00 /ሃያ ሁለት ሺህ /ብር
ሐ. ሎት3.የደንብ ልብስ 20000.00 / ሃያ ሺህ/ብር
መ. ሎት4. የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት 5000.00 /ሶስት ሺህ/
ሠ. ሎት5. የትራንስፖርት አገልግሎት 10000.00 /አስር ሺህ /
ረ. ሎት.6 የመኪና መለዋወጫ 15000/ አስራ አምስት ሺህ/
ሰ. ሎት7 የቋሚ ዕቃ 5000/አምስት ሺህ/ብር
ሸ. ሎት.8 የህትመት አገልግሎት 10000/ አስር ሺህ/ብር
ቀ. ሎት.9 መስተንግዶ አገልግሎት 20000/ ሃያ ሺህ/ብር
በ. ሎት 10 የፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት 10000/ አስር ሺህ/ብር
ተ. ሎት 11 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት10000/አስር ሺህ/ብር ብቻ በባንክ በተመሠከረለት CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
14.የጨረታውን ዝርዝር የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ኮፒ በየሎቱ የማይመለስ ብር 250/ሁለት መቶ ሃምሳ/ ብር በመክፈል ከፋ/ጽ/ቤት አሮጌ ህንጻ 1ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፡፡
አድራሻችን በጉለሌ ክ/ከ/ወ/1 ፋ/ጽ/ቤት በተለምዶ ሽሮሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ቁስቋም በሚወስደው መንገድ ላይ ሲሆን
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111 230 753 / 0111 540 864 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ ፡፡
ማሳሰቢያ ፡- - እያንዳንዱ ተጫራች በሚያቀርበው ዋጋ ላይ የቫት ተመዝጋቢ ሆኖ ካልጨመረ እንደተጨመረ ተደርጎ ስለሚወሰድ VAT በመጨመር ሰነዱ ይቅረብ ፡፡
፡-የትራንስፖርት አገልግሎትን በተመለከተ፤ የቫት/ቲኦቲ ተመዝጋቢ ሆኖ ካልጨመረ እንደተጨመረ ተደርጎ ስለሚወሰድ VAT/ ቲኦቲ በመጨመር ሰነዱ ይቅረብ ፡፡
በጉለሌ ክ/ከ/ወረዳ‐1 ፋ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-17
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ጠዋት 3፡30
- Bid opening: 2026-09-17 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gulele Sub city Woreda 1 FEDB
- Buyer address: በተለምዶ ሽሮሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ቁስቋም በሚወስደው መንገድ ላይ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 250.00 ብር በየሎቱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
- Posted at: 2026-09-05T08:00:59.000Z