Equipment and Accessories

ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር የጀነሬተር አውቶማቲክ ትራንስፈር (ATS) እቃዎች ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ከዚህ በታች የዘረዘርናቸው የጀነሬተር አውቶማቲክ ትራንስፈር (ATS) እቃዎች አጠቃላይ መመሪያዎች እና ግዴታዎች

1. ይህ ማስተወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ አቅራቢያቸው የሚያቀርቡት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር ጠዋት 3:00 እስከ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ቅጽ ላይ በመሙላት ለጨረታ ማስረከቢያ ያቀረቡበትን ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በCPO ብቻ በማስያዝ የድርጅቱ የፋሲሊቲና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

2. በዚሁ የግዥ ጨረታ የሚቀርቡ ሰነዶች በሙሉ በአማረኛ ወይም እንግሊዘኛ ቋንቋ መጻፍ አለባቸው።

3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፍል ከድርጅቱ ገንዘብ ተቀባዮች ቢሮ መግዛት ይቻላል።

4. ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላ ዘግይተው የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

5. ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በድርጅቱ የሠራተኞች ክበብ ውስጥ ይከፈታል።

6. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመክፈል መፈጸም ይኖርባቸዋል።

7. በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ያሸነፈባቸው እቃዎች የማያነሱ ከሆነ ለጨረታ ማስረከቢያ የተያዘው ወደ ድርጅቱ ገቢ ይሆናል።

8. የጨረታ ተሸናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለጨረታው ያስያዙት CPO ተመላሽ ይደረግላቸው።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

N.0

Description

Model

Three phases

Qty

Status

1

Manual transfer Switch

CTI63

Three phases

15

New

2

Manual transfer Switch

CTI100

Three phases

16

New

3

Manual transfer Switch

CTI160

Three phases

14

New

4

Caterpillars Olympias Generator

Ghe250-2

Three phases

1

Old

ስልክ ቁጥር 0114 421133 የውስጥ መስመር 212 ወይም 223 ደውሱ
መጠየቅ ይቻላል።

ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-09-14
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር ጠዋት 3:00 እስከ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-15 10:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር ጠዋት 3:00 እስከ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ቆይቶ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ries Engineering S.C.
  • Buyer address: DEBEREZEIT ROAD ADDIS ABABA
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T08:13:24.000Z
← Back to all tenders