Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 10 ፋ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተገለጹትን ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ (CPO) ብር መጠን በየሎቱ ማስያዝ አለባቸው።

  1. ሎት 1አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
  2. ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
  3. ሎት 3 የደንብ ልብስ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  4. ሎት 4 ቋሚ እቃ 100,000 አንድ መቶ ሺህ ብር)
  5. ሎት 5 የትራንስፖርት አገልግሎት 10,000 (አስር ሺህ ብር)
  6. ሎት 6 የህትመት ውጤቶች እና የዲኮር ስራዎች 10,000 (አስር ሺህ ብር
  7. ሎት 7 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና (እንስታሌሽን 1,000 (አንድ ሺህ ብር)
  8. ሎት 8 የደንብ ልብስ ስፌት 1,000 (አንድ ሺህ ብር)

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው

9. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

10, የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

11. በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤

12. የጨረታ ሰነዳቸውን ገዥ ባዘጋጀው ስፔስፍኬሽን መሠረት ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፤

13. ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎችና አገልግሎት የወቅቱን ምርት ናሙና ማቅረብ አለባቸው። 

1. የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ አድርገው በሁለት ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒውን ማቅረብ

2. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትንና የመጓጓዣ ወጪን ጨምሮ መሆን አለበት፤

3. ግዥው በየሎቱ በተጠቀሱት እቃዎችና አገልግሎት ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት ይኖረዋል፤

4. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 400 ብር እየከፈሉ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከወረዳው ፋ/ጽ/ቤት 4ተኛ ፎቅ መግዛት ይቻላል፤

5. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰአት በጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቦታ ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል፤

6. ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ተጫራቾች የሰጡት ዋጋ ለ60 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፤

7. ተጫራቾች የአሸነፉበት ዕቃ ውል በፈጸሙ በ5 ቀን ውስጥ እቃውን ንብረት ክፍል ገቢ አድርገው ክፍያ መጠየቅ ይኖርባቸዋል፤

8. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ ፡-

  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0118931464 መጠቀም ይችላሉ።
  • ልዩ ቦታው መሪ ከሴንተራል ሆቴል 200 ሜትር በስተቀኝ በኩል ገባ ብሎ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-14
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-15 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lemi Kura Sub City Woreda 10 Finance office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T08:39:54.000Z
← Back to all tenders