Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የሲዳማ ብ/ክ መንግሥት እርሻና ተፈ/ሀ/ልማት ቢሮ የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት እርሻና ተፈ/ሀ/ልማት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዥዎችን ከዚህ በታች በቀረበው መሰረት፡-

  • ሎት 1. የፅሕፈት መሳሪያ /እስቴሽነሪ/
  • ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3 . የኤሌክትርኒክስ ዕቃዎች
  • ሎት 4. የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክስ
  • ሎት 5 ፈርኒቸር የቢሮ ዕቃዎች ግዥ በህጋዊ ተጫራቾቾ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው

2. ለአቅራቢነት የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

3. ተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ

4 የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬትና መለያ ቁጥር ያለው

5. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የግብር ከፋይነት ማስረጃ የሚያቀርቡ

6. ለእያንዳንዱ የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫዎች እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ። ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ሁለት ሁለት መቶ ብር/200/ ከፍሎ መግዛት አለባቸው።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ከጠቅላላ ዋጋ

  • ሎት 1. የፅሕፈት መሳሪያ እስቴሽነሪ 30,000
  • ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች 10,000
  • ሎት 3 . የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 50,000
  • ሎት 4. የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል 50,000
  • ሎት 5. ፈርኒቸር የቢሮ ዕቃዎች 50,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለበት።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉን ቴክኒካልና ፋይናንሻል አንድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና ጠቅላላውን በአንድ ሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማጠቃለል ማቅረብ አለባቸው።

9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ግዥ ፋ/ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡።

11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው ግዥ ፋ/ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት በስልክ ቁፕር 046 221 2413 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የሲዳማ ብ/ክ መንግሥት እርሻና ተፈ/ሀ/ልማት ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-21
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-21 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Sidama National Regional State Agriculture & Natural Resource Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T08:42:11.000Z
← Back to all tenders